Get Mystery Box with random crypto!

ጥቁር ምንጣፍ ወይስ አስፋልት ያስባለው አነጋጋሪው የህንድ አስፋልት በህንድ ማሃራሽትራ ግዛት | ሰሌዳ | Seleda

ጥቁር ምንጣፍ ወይስ አስፋልት ያስባለው አነጋጋሪው የህንድ አስፋልት

በህንድ ማሃራሽትራ ግዛት ጃልና የተሰኘው ወረዳ ነዋሪዎች ለአመታት የመንገድ ይገንባልን ጥያቄ በቅርቡ ምላሽ አግኝቷል። ነገር ግ ደስታቸውን የቅጽበት ሆኖ እንዲቀር የሚያደርግ ክስተት ገጥሟቸዋል ይላል የአልዐይን ዘገባ።

የጠጠር መንገዳቸው የለበሰው አስፋልት በቀላሉ እንደምንጣፍ ሊነሳ የሚችል በሌላ ቋንቋም ጥቁር ምንጣፍ ሆኖ አግኝተውታል።

በእጃቸው ሲያነሱትም ከስሩ ጨርቅ ነገር ለብሶ ከላዩ ላይ በስሱ አሽዋና ሬንጂ ተደርጎበት የተሰራ መሆኑንም ያረጋግጣሉ። መንገዱን የሰራውን ተቋራጭ ሲጠይቁት አዲስ የጀርመን ቴክኖሎጂ ተጠቅሜያለሁ ሲል ተሳልቋል።