Get Mystery Box with random crypto!

ሰሌዳ | Seleda

የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የሰርጥ አድራሻ: @seledadotio
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.47K
የሰርጥ መግለጫ

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@seleda_support ለማንኛውም አይነት ጥያቄ

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-07-07 11:20:43
የምድራችን የምንጊዜም "እድሜ ጠገቡ" ውሻ

በፖርቹጋል የሚገኘው ‘ቦቢ’ የተባለው የ31 ዓመቱ ውሻ በእድሜ ትልቁ ውሻ በመሆን በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ስሙ ሰፍሯል።

ውሻው በፖርቹጋል ‘ራፌይሮ ዶ አሌንቲዮ’ የሚል ስያሜ ከተሰጣቸው የውሻ ዝርያዎች የተገኘ ሲሆን እነዚህ ውሻዎች አማካይ እድሜያቸው ከ12 እስከ 14 ዓመት ነው ተብሏል፡፡

ቦቢ በፈረንጆቹ ሰኔ 11 ቀን 1992 የተወለደ ሲሆን በትናንትናው እለት በእድሜ ትልቁ ውሻ በመባል የዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ስሙ ሰፍሯል፡፡

Via - FBC
4.8K views08:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-07 09:45:23
ቲክቶክ "ቲክቶክ ሚዩዚክ" የተሰኘ አዲስ መተግበሪያ አስጀመረ!

ባይት ዳንስ ቲክቶክን በባለቤትነት የሚያስተዳድረው ድርጅት አዲስ "ቲክቶክ ሚዩዚክ" የተሰኘ መተግበሪያ ስራ ጀመረ።

ይህ ስፖቲፋይን ይፎካከራል የተባለው "ቲክቶክ ሚዩዚክ" ትናትና በብራዚል እና በኢንዶኔዥያ ስራ እንደጀመረ እየተነገረ ነው ።

አሉ የተባሉ የቅጅ ድርጅቶችን ልክ እነ Universal Music Group ፣ Warner Music Group እና Sony Music ስር ያሉ ሙዚቃዎችንም አካቷል።

ይህ መተግበሪያ ቲክቶክ ላይ የሚታወቁትንም ሙዚቃዎችን በሙሉ ርዝመት ያጫውታል።

ባይት ዳንስ ከዚህ ቀደም "ሬሶ" የተባለውን ስትሪሚንግ አገልግሎቱን አቋርጦ በ "ቲክቶክ ሚዩዚክ" እንደሚተካ አሳውቋል።

ምንጭ፦ TechCrunch
5.0K viewsedited  06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-07 09:35:56
የኢትዮጵያ ተጨዋቾች የዝውውር መስኮት በሚቀጥለው ሳምንት በይፋ ይከፈታል

የኢትዮጵያ ወንዶች እና ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ከሐምሌ ስምንት ጀምሮ ክፍት እንደሚሆን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

መስከረም 25/2016 ድረስ የሚቆየው ዝውውር መስኮቱ የተጫዋቾች ዝውውር ህጋዊነት የሚፀድቀው በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፅሕፈት ቤት ተገኝቶ በመፈራረም ብቻ መሆኑን አሳስቧል።

በክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች በሌላ አካል በኩል የሚደረግ ስምምነት ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ጨምሮ ፌዴሬሽኑ በመረጃው አሳውቋል።

ምንጭ - የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
4.9K views06:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-07 09:03:42
ቱጃሮቹ ቡጢ ለመግጠም ቀን ቢቆረጥላቸውም ፍጥጫው ግን ከወዲሁ አይሏል

ከትናንት በስተያ የተጀመረው Threads የተባለው አዲሱ የሶሻል ሚዲያ ፕላትፎርም ይፋ በተደረገ በአንድ ሰአት ውስጥ አምስት ሚሊየን ተጠቃሚ አፍርቷል። 24 ሰአት ሳይሞላም የተጠቃሚው ቁጥር ከሰላሳ ሚሊየን በላይ አልፏል።

ይህ ከሆነ ከሰአታት በኋላም ኤለን መስክ በጠበቃው በኩል ዙከንበርግ ላይ ክስ እንደመሰረተ አስታውቋል። የክሱ ሃሳብ ደሞ በቀድሞ የትዊተር ሰራተኞች በኩል የስራ ሚስጥሬን ተዘርፌያለሁ ነው።

ኤለን መስክ ልክ ትዊተርን እንደገዛ ያደረገው ነገር 80% የሚሆነውን ሰራተኛ ከትዊተር ማባረር ነበር። እና ዙከርበርግ ከትዊተር ከተባረሩት ውስጥ አብዛኛዎቹን ሰራተኞች ቀጠራቸው። 

እናም ዛሬ ከ 8ሺህ ሰራተኛ ስድስት ሺውን ጠራርጎ አባሮ፤ ያባረርኳቸው ሰራተኞቼ ሚስጥሬን ለተፎካካሪ ሰጠውብኛል ማለት ያስኬዳል ድሮስ በግፍ ያባረራቸው ሰራተኞች ፡ ለሱ ጥቅም እንዲጠነቀቁለት ጠብቆ ነበር

የጣልኩትን ሲያነሱብን አልወድም

Via - Wasihune Tesfaye
5.0K views06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 19:31:17
ተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ እና ውርጃን የሚያወግዝ ሰልፍ በሐዋሳ ከተማ ተካሄደ

በሐዋሳ ከተማ የሚገኙ 22 የቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን የተወጣጡ ሰልፈኞች ከኃይማኖት እና ከባህል ያፈነገጡ ተግባራትን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አድርጓል።

ግብረሰዶማዊነትን፣ ወርጃን፣ ነብስ ማጥፋትን፣ ምንዝርና እና ሱሰኝነትን እንቃወማለን የሚሉ መፈክሮች በሰላማዊ ሰልፉ ላይ መንፀባረቃቸውን የደቡብ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ዘግቧል።
4.5K views16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 19:11:26
የኢትዮጵያ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ባለፉት አምስት ዓመታት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን እንዳጓጓዘ አስታወቀ

በቻይና ብድር የተገነባው. የኢትዮጵያ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ባለፉት አምስት ዓመታት 1 ሺህ 824 ጊዜ የመንገደኞች ማመላለሻ ባቡሮች እንደተመላለሱበት የትራንስፖርት ሚንስትሩ ዓለሙ ስሜ መናገራቸውን ጠቅሶ ዥንዋ ዘግቧል።

የባቡሩ ትራንስፖርቱ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ 530 ሺህ 900 መንገደኞችን በ6 ሺህ 133 የካርጎ ባቡር ምልልሶች ከ7 ሚሊዮን 328 ሺህ ቶን በላይ ሸቀጦችን ማጓጓዙን ሚንስትሩ መግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ዓለሙ ይህን የተናገሩት፣ በኢትዮጵያና ቻይና የቤልት ሮድ ፕሮጀክት ዙሪያ በተደረገ የጋራ ውይይት ላይ እንደኾነ ተገልጧል።
4.6K views16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 18:54:03
አትሌት ገንዘቤ በአንትሪም ኮስት ግማሽ ማራቶን እንደምትሳተፍ  አስታወቀች

አትሌት ገንዘቤ በማኅበራዊ ትስስር ገጿ ባሰፈረችው መልዕክተት ነሐሴ 27 በሚካሄደው የአንትሪም ኮስት ማራቶን እንደምሳተፍ ስገልፅ በከፍተኛ ደስታ ነው ብላለች፡፡

ከዚህ በፊት በአየርላንድ አንተሪም ኮስት ተሳትፋ እንደማታውቅም ነው የገለጸችው፡፡ አድናቂዎቿ በተጠቀሰው ቀን እና ቦታ ተገኝተው እንዲያበረታቷትም ጠይቃለች፡፡
4.4K views15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 18:40:26
Summer Python Programming.

ልጆችዎ በዚህ ክረምት መሰረታዊ የፕሮግራሚንግ እውቀት እንዲያገኙ ይፈለጋሉ?

የቴክኖሎጂ ተቀባይ ብቻ ሳይሆን የቴክኖሎጂ ፈጣሪ ለመሆን የፕሮግራሚንግ እውቀት ወሳኝ መሆኑንስ ያውቃሉ?

ኑ መሰረታዊውን የ21ኛው ክፍለ ዘመን ክህሎት እናስተዋውቆ::

በኮዲንግ ላይ ምንም አይነት እውቀት ወይንም የቀድሞ ልምድ አያስፈልግም, ፈላጎት ብቻ በቂ ነው

መሰረታዊ የፕሮግራሚንግ እውቀት, ለጀማሪ በሚሆን መልኩ የተዘጋጀ

ብቁ በሆኑ መምህራን

በተመጣጣኝ ዋጋ በ ወር 2000 ብር ብቻ


አድራሻ : 4 ኪሎ
በ ሳምንት 3 ሰዓት


ለመማር ማስተማር ስርአቱ ጥራት ሲባል ውስን ተማሪዎች ስለምናስተናገድ ፈጥነው ይመዝገቡ

ለመመዝገብ ከታች ያለውን link ይጠቀሙ ወይም ይደወሉልን

Register now: https://forms.gle/b1pU3C4C6GC61zmw5

ለበለጠ መረጃ :
@Abukiab or 0934170179


ፈጥነው ይመዝገቡ
4.2K views15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 18:39:59
ፈንድቃ እንዲቆይ ፍቃድ ተሰጠው

ከ20 ዓመታት በላይ የኢትዮጲያን ባህል ለዓለም የማሳወቅ ስራን ሲሰራ የነበረው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ከሰሞኑ እንዲፈርስ መወሰኑ ቅሬታ አስነስቶ ነበር።

ይፈርሳል የተባለው ፈንድቃ የባህል ቤት ውሳኔው ተቀይሮ ዛሬ ባለቤቱ አርቲስት መላኩ በላይ እንድገለፀው "የአዲስ አበባ ከንቲባ ድምጻችንን ሰምተው ፈንድቃን እንድናቆይ ፍቃድ እንደሰጡን ላበስራችሁ ፈልጋለሁ" ብሏል።
3.7K views15:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 18:31:59
12 ኛው ዙር አድማስ ዲጂታል ሎተሪ የአሸናፊዎች እጣ ወጣ!

በ1ኛ እጣ 3 ሚሊየን ብር የሚያሸልመው አድማስ ሎተሪ የእድለኞች እጣ ዛሬ ይፋ ሆነዋል ሎተሪውን ከቀጣዩ ዙር ጀምሮ ሽልማቱን ወደ 4 ሚሊየን ያሳድጋል ተብሏል።
3.7K views15:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ