Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ባለፉት አምስት ዓመታት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን እንዳጓጓዘ | ሰሌዳ | Seleda

የኢትዮጵያ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ባለፉት አምስት ዓመታት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን እንዳጓጓዘ አስታወቀ

በቻይና ብድር የተገነባው. የኢትዮጵያ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ባለፉት አምስት ዓመታት 1 ሺህ 824 ጊዜ የመንገደኞች ማመላለሻ ባቡሮች እንደተመላለሱበት የትራንስፖርት ሚንስትሩ ዓለሙ ስሜ መናገራቸውን ጠቅሶ ዥንዋ ዘግቧል።

የባቡሩ ትራንስፖርቱ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ 530 ሺህ 900 መንገደኞችን በ6 ሺህ 133 የካርጎ ባቡር ምልልሶች ከ7 ሚሊዮን 328 ሺህ ቶን በላይ ሸቀጦችን ማጓጓዙን ሚንስትሩ መግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ዓለሙ ይህን የተናገሩት፣ በኢትዮጵያና ቻይና የቤልት ሮድ ፕሮጀክት ዙሪያ በተደረገ የጋራ ውይይት ላይ እንደኾነ ተገልጧል።