Get Mystery Box with random crypto!

ቱጃሮቹ ቡጢ ለመግጠም ቀን ቢቆረጥላቸውም ፍጥጫው ግን ከወዲሁ አይሏል ከትናንት በስተያ የተጀመ | ሰሌዳ | Seleda

ቱጃሮቹ ቡጢ ለመግጠም ቀን ቢቆረጥላቸውም ፍጥጫው ግን ከወዲሁ አይሏል

ከትናንት በስተያ የተጀመረው Threads የተባለው አዲሱ የሶሻል ሚዲያ ፕላትፎርም ይፋ በተደረገ በአንድ ሰአት ውስጥ አምስት ሚሊየን ተጠቃሚ አፍርቷል። 24 ሰአት ሳይሞላም የተጠቃሚው ቁጥር ከሰላሳ ሚሊየን በላይ አልፏል።

ይህ ከሆነ ከሰአታት በኋላም ኤለን መስክ በጠበቃው በኩል ዙከንበርግ ላይ ክስ እንደመሰረተ አስታውቋል። የክሱ ሃሳብ ደሞ በቀድሞ የትዊተር ሰራተኞች በኩል የስራ ሚስጥሬን ተዘርፌያለሁ ነው።

ኤለን መስክ ልክ ትዊተርን እንደገዛ ያደረገው ነገር 80% የሚሆነውን ሰራተኛ ከትዊተር ማባረር ነበር። እና ዙከርበርግ ከትዊተር ከተባረሩት ውስጥ አብዛኛዎቹን ሰራተኞች ቀጠራቸው። 

እናም ዛሬ ከ 8ሺህ ሰራተኛ ስድስት ሺውን ጠራርጎ አባሮ፤ ያባረርኳቸው ሰራተኞቼ ሚስጥሬን ለተፎካካሪ ሰጠውብኛል ማለት ያስኬዳል ድሮስ በግፍ ያባረራቸው ሰራተኞች ፡ ለሱ ጥቅም እንዲጠነቀቁለት ጠብቆ ነበር

የጣልኩትን ሲያነሱብን አልወድም

Via - Wasihune Tesfaye