Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ተጨዋቾች የዝውውር መስኮት በሚቀጥለው ሳምንት በይፋ ይከፈታል የኢትዮጵያ ወንዶች እና | ሰሌዳ | Seleda

የኢትዮጵያ ተጨዋቾች የዝውውር መስኮት በሚቀጥለው ሳምንት በይፋ ይከፈታል

የኢትዮጵያ ወንዶች እና ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ከሐምሌ ስምንት ጀምሮ ክፍት እንደሚሆን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

መስከረም 25/2016 ድረስ የሚቆየው ዝውውር መስኮቱ የተጫዋቾች ዝውውር ህጋዊነት የሚፀድቀው በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፅሕፈት ቤት ተገኝቶ በመፈራረም ብቻ መሆኑን አሳስቧል።

በክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች በሌላ አካል በኩል የሚደረግ ስምምነት ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ጨምሮ ፌዴሬሽኑ በመረጃው አሳውቋል።

ምንጭ - የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን