Get Mystery Box with random crypto!

ሰሌዳ | Seleda

የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የሰርጥ አድራሻ: @seledadotio
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.47K
የሰርጥ መግለጫ

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@seleda_support ለማንኛውም አይነት ጥያቄ

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-05-18 10:41:01
ዲቪ 2023 የደረሰን ሰዎች ሊቃጠልብን ነው» ባለ እድለኞች

የ2023 የዲቪ ሎተሪ ባለዕድል ከሆኑት መካከል እስካሁን ኤምባሲው ለ123 ሰዎች ሂደቱን ጨርሶ ቪዛ እንደሰጠ፣ የ130 ሰዎች የቪዛ ጥያቄያቸው እየታየ መሆኑን እንዲሁም ሌሎች 130 ባለዕድሎች ደግሞ ሂደቱን መጀመራቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።

ከ2761 ዕድለኞች ውስጥ ለ383 ሰዎች ብቻ ነው ሂደቱ የተጀመረላቸው ወይንም ያለቀላቸው። ኤምባሲው በወር ውስጥ እያስተናገደ ባለው የሰው ቁጥር መሰረት 2200 የሚሆኑት ሰዎች ዕድላቸው ወደ መቃጠል እየሄደ ነው” ይላል አቶ አያና የዲቪ 2023 እድለኛ ስጋቱን ሲገልፅ።

አቶ ሙሉቀን ጣሰው በበኩሉ የዲቪ ሎተሪ ዕድለኛ መሆኑን ባወቀ ጊዜ እርሱም ሆነ ቤተሰቦቹ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቷቸው እነደነበር ያስታውሳል።

የባንክ ማናጀር የነበረው ሙሉቀን የዲቪ እንደደረሰው ካወቀ በኋላ “ወደ አሜሪካ በቅርቡ እሄዳለሁ በሚል ተስፋ ሥራዬን ለቅቄ በግል ሥራ ላይ አትኩሬ ነበር” በማለት አሁን ግን ይህ ዕድል ወደ ሊቃጠል ይችላል በሚል ስጋት ውስጥ መሆኑን ተናግሯል።

“አሁን አሁን ሳስበው ምናለበት የዲቪው ሎተሪው ባይወጣልኝ ብዬ እያሰብኩ ነው። ቤተሰቦቼ እና ጓደኞቼ መቼ ነው የምትሄደው እያሉ ይጠይቁኛል። ይህ ዕድሌ ከተቃጠለ እዚህ ከተማ ውስጥ መኖር አልችልም” ይላል ሙሉቀን።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ለቢቢሲ በሰጠው ምላሽ፣ ላለፉት ሦስት ዓመታት በኮቪድ እና በሌሎች ችግሮች ምክንያት በርካታ ውዝፍ ሥራዎች ስለነበሩበት በሚፈለገው ሁኔታ የዲቪ ሎተሪ ዕድለኞችን ለማስተናገድ እንዳልቻለ ገልጿል።

ለዲቪ ዕድለኞች የቪዛ መስጠት ሂደት “በአጭር ጊዜ ውስጥ በአስቸኳይ የሚከናወን ሥራ ስላልሆነ” በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ሁሉንም የዲቪ ዕድል አሸናፊዎች ማስተናገድ እንደማይቻልም ገልጿል።
6.0K views07:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 08:10:24
#ዘይገርም

ኤለን መስክ በ2023 ሴብቴምበር ወር የሮቦት ሚስት መሸጥ እንደሚጀምር አስታውቋል

ቱጃሩ ሰው ራሱም ከሮቦት ጋር እንደሚሞሸር ታውቋል። ኤለን መስክ የሮቦት ሚስቱን ካታኔላ ሲል ጠርቷታል።

የሮቦት ሚስቶች ጋር ወሲብ ለመፈፀም ፓስዋርድ፤ ፓተርን ወይም በኣሻራ መክፈት ግድ ይላል። ይህም ሮቦቷ እንዳትደፈር ወይም ቺት እንዳታረግብህ ይጠቅማል ተብሏል።

አንድ የሮቦት ሚስት ቻርጅ ለመደረግ 3 ቀን ይፈጅባታል። አፍሪካ ላይ በ2023 ኖቬምበር ወር ሽያጩ ይጀመራል።

የሰው ልጅ ኣደጋ ውስጥ ነው። አሊታ ሚለው አኒሜሽን ፊልም የእውነት ሆኗል።

Via - Erimias belayineh
6.7K views05:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 07:54:16
የፌደራል መንግስት “ደመወዝ የመክፈል ጫና ውስጥ ለገቡ” ክልሎች፤ ከሰባት ቢሊዮን ብር በላይ ማበደሩን የገንዘብ ሚኒስትሩ ተናገሩ

የክልል መንግስታት ላጋጠማቸው የበጀት እጥረት፤ የፌደራል መንግስት ብድር መስጠት እንጂ ቀጥታ ድጋፍ ማድረግ እንደማይችል የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተናረዋል። የፌደራል መንግስት “ደመወዝ የመክፈል ጫና ውስጥ ለገቡ” ክልሎች፤ ከሰባት ቢሊዮን ብር በላይ ማበደሩንም ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት፤ ትላንት ረቡዕ ግንቦት 9፤ 2015 ከተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ ላይ ነው።

Via - Ethiopia insider
6.0K views04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 00:03:19
ማንችስተር ሲቲ የኢስታንቡሉን ትኬት ቆርጧል

ማንችስተር ሲቲ ከሪያል ማድሪድ ጋር ያደረገውን የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ 4 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን ማንችስተር ሲቲ ሪያል ማድሪድን በድምር ውጤት 5 ለ 1 በማሸነፍ ለፍፃሜ ማለፉን አረጋግጧል።

ማንችስተር ሲቲ የፍፃሜ ጨዋታውን ከጣልያኑ ክለብ ኢንተር ሚላን ጋር ቱርክ ኢስታንቡል ላይ የሚያደርጉ ይሆናል።
6.6K views21:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 20:34:20
ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት አራተኛውን አገር ዓቀፍ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ልታካሂድ ነው ተባለ።

የኢትዮጵያ ፕላንና ልማት ሚንስቴር በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት አራተኛውን አገር ዓቀፍ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ለማካሄድ ማቀዱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት ላይ መናገሩን የመንግሥት ዜና አውታሮች ዘግበዋል።

መንግሥት ቆጠራውን በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት የልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅዱ እንዳካተተው ሚንስቴሩ መግለጡን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። በአገሪቱ በየአስር ዓመቱ የሕዝብና ቤት ቆጠራ እንደሚደረግ በሕግ ቢደነገግም፣ የመጨረሻው ቆጠራ 20 ዓመታት ሊደፍን ተቃርቧል።
6.9K views17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 17:49:18
አንዳች ድራማዊ ክስተት የማያጣው የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሜር ሊግ

ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀዋሳ ከተማ ከደቂቃዎች በፊት ጨዋታ አድርገው ነበር 1 ለ 0 በቅዱስ ጊዮርጊስ መሪነት ጨዋታው 70ኛ ደቂቃ ደረሰ።

የመሃል ዳኛው በዓምላክ ተሰማ በቅዱስ ጊዮርጊስ ግብ ክልል ውስጥ ጥፋት ተፈፅሟል በማለት ለሀዋሳ የፍፁም ቅጣት ምት ይሰጣሉ።

ይሄኔ በጣም የተደሰተው የሀዋሳ ተጫዋች አብዱልባሲጥ ዳኛውን ለረጅም ጊዜ እንደተነፋፈቀ ሰው አፈፍ አድርጎ አቅፎ ይስመዋል። በድርጊቱ የተበሳጨው ዳኛ በአምላክ ተጨዋቹን ወርውሮታል። ጨዋታው አንድ እኩል በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
7.2K views14:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 17:23:51
በመጋቢት ወር ሀገራዊ አጠቃላይ የፍጆታ እቃዎች የዋጋ ግሽበት 33.7 በመቶ ደርሷል ት

በመጋቢት ወር ሀገራዊ አጠቃላይ የፍጆታ እቃዎች ዋጋ ግሽበቱ 33.7 በመቶ መድረሱን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታዉቋል። በወሩ የምግብ ነክ ፍጆታዉም 34.5 በመቶኛ መድረሱን ሚኒስትሩ ጠቁሟል።

በተመሳሳይ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ዋጋ ግብበቱ 32.5 በመቶ ላይ ይገኛል ተብሏል። ግሽበቱ በህብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጫና እያሳደረ መሆኑን ሚኒስቴሩ አህመድ ሽዴ አልሸሸጉም።
6.7K views14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 14:49:42
ዛሬ ምሽት 4 ሰአት የሁሉም እግርኳስ ወዳድ አይን ኢትሀድ ላይ የሚደረገውን የዝሆኖች ፍትጊያ ላይ ይተከላል።

የካርሎ አንጀሎቲው ሪያል ማድሪድ እንደለመደው ዋንጫን አይቶ ወደኃላ አለማለቱን ይደግም ይሆን

ወይንስ የፔፕ ጋርድላው ማንችስተር ሲቲ በዘንድሮ አመት በኢትሀድ ያለመሸነፍ ሪከርዱን አስጠብቆ ለፍፃሜ ይደርሳል የሚለውን ጥያቄ መልስ ለማግኘት ምሽት 4ሰአት መጠበቅ ግድ ይላል
6.9K views11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 14:22:25
ሙዓለ ንዋይ ገበያ ለማቋቋም አንድ ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ታወቀ

የኢትዮጵያ ‹‹የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ›› ለማቋቋም አንድ ቢሊዮን ብር ገደማ የመነሻ ካፒታል ያስፈልጋል መባሉን ሪፖርተር ጽፏል፡፡ ከገበያው መንግሥት 25 በመቶ የግል ኢንቨስተሮች ደግሞ 75 በመቶ ድርሻ ይኖራቸዋል ተብሏል።

በ2016 ዓ.ም. ወደ ሥራ የሚገባው የሙዓለ ንዋይ ገበያው ትርፍ ለማስመዝገብ ከሦስት እስከ አራት ዓመታት እንደሚፈጅበት፣ በጥናት መታወቁን የሪፖርተር ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ ለግል ኢንቨስተሮች አክሲዮን የመሸጥ ሥራ ማክሰኞ ግንቦት 8 ቀን 2015 ዓ.ም. በይፋ ተጀምሯል፡፡
6.6K views11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 12:51:22
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ደስተኛ ያልሆነው ዲኤስ ቲቪ ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ የሊጉን የቀጥታ ስርጭት ላቋርጠው እችላለሁ ማለቱ ተሰማ

የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ያለፉትን ሶስት አመታት ዲኤስ ቲቪ በሱፐር ስፖርት የቀጥታ ስርጭትን እያገኘ ለእግር ኳሳችን አንድ ደረጃ መሻገር የራሱን አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል።

ይሁን እና የዘንድሮው የ2015 የሊጉ ጨዋታዎች በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ምክንያቶች የቀጥታ ስርጭት በመሐል ሲቋረጥ ሲስተዋል የነበረ ሲሆን ኢትዮ ፉት አሁን በደረሳት መረጃ ከሆነ ከቀጣዩ የ24ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ጀምሮ የሊጉ ጨዋታዎች የቀጥታ ስርጭትን ሊያቋርጥ መሆኑን ታውቋል።

ምንጭ- ኢትዮ ፉት ስፖርት
6.7K views09:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ