Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት አራተኛውን አገር ዓቀፍ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ልታካሂድ ነው ተባለ። | ሰሌዳ | Seleda

ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት አራተኛውን አገር ዓቀፍ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ልታካሂድ ነው ተባለ።

የኢትዮጵያ ፕላንና ልማት ሚንስቴር በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት አራተኛውን አገር ዓቀፍ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ለማካሄድ ማቀዱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት ላይ መናገሩን የመንግሥት ዜና አውታሮች ዘግበዋል።

መንግሥት ቆጠራውን በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት የልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅዱ እንዳካተተው ሚንስቴሩ መግለጡን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። በአገሪቱ በየአስር ዓመቱ የሕዝብና ቤት ቆጠራ እንደሚደረግ በሕግ ቢደነገግም፣ የመጨረሻው ቆጠራ 20 ዓመታት ሊደፍን ተቃርቧል።