Get Mystery Box with random crypto!

ሰሌዳ | Seleda

የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የሰርጥ አድራሻ: @seledadotio
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.39K
የሰርጥ መግለጫ

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@seleda_support ለማንኛውም አይነት ጥያቄ

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2023-05-11 08:45:18
ሳፋሪኮም  ኢትዮጵያ የሞባይል መኒ (MPESA) ፈቃድ አገኘ

በኢትዮጵያ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ዛሬ አንድ ዓመት የሞላው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል መኒ (MPESA) ፈቃድ ማግኘቱን አስታውቋል።

የሳፋሪኮም ኬንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር ፒተር ንዴግዋ ዛሬ ግንቦት 3 ቀን 2015 ዓ ም ንጋት ላይ የተቋማቸውን ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ለባለድርሻ አካላት ሪፖርት ሲያቀርቡ እንዳስታወቁት፣ በኢትዮጵያ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ አንድ ዓመት የሞላው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የድጅታል ፋይናንስ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን ሞባይል መኒ ፈቃድ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማግኘቱን አስታውቀወል። ወሚቀጥሉት ሳምንታት አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርም ጠቁመዋል።
6.9K views05:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 19:31:07
ባለስልጣኑ ትምህር ቤቶች ከወላጆች ጋር በቂ መግባባት ላይ ሳይደርሱ የክፍያ ጭማሪ እንዳያደርጉ አስጠነቀቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በከተማ አስተዳደሩ ሥር ለሚገኙ የግል እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ትምህርት ቤቶች በጻፈው ደብዳቤ፤ በ2016 የትምህር ዘመን የክፍያ ጭማሪ ከወላጆች ጋር በቂ መግባባት ላይ ሳይደርስ ወደ ተግባር መግባት እንደማይቻል ያሳሰበ ሲሆን፤ ባለው አሰራር መሰረት ከተማሪ ወላጅ ተወካዮች እና ከባለስልጣን መ/ቤቱ ጋር ውይይት በማድረግ በሚቀመጠው የጋራ አቅጣጫ መሰረት ብቻ ወደ ተግባር የሚገባ መሆኑን አክሏል።
7.5K views16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 17:42:41
የውጭ ኢንቨስተሮች በቢሮክራሲና በሙስና ሳቢያ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች እየወጡ መሆናቸው ተነገረ

በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ የውጭ ባለሀብቶች ከአስፈጻሚው አካል በሚጠየቅ ያልተገባ የጉዳይ ማስፈጸሚያ ክፍያና በቢሮክራሲ ማነቆ በመማረራቸው፣ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ለቀው እየወጡ መሆኑን ሪፖርትር ጽፏል፡፡

ይህ የተገለጸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንን የ2015 ዓ.ም. የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሰኞ ሚያዝያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ሲገመግም ነው፡፡

በሌብነት፣ በዘረፋና በቢሮክራሲ ማነቆ የተነሳ ከኢስተርን ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ 51 ባለሀብቶች ለቀው መውጣታቸውን በመስክ ምልከታው ማረጋገጣቸውን የቋሚ ኮሚቴው አባላት አስረድተዋል፡፡

ከፓርኩ የለቀቁ ባለሀብቶች ከአገር በመውጣት ወደ ኡጋንዳና ሌሎች ጎረቤት አገሮች፣ እንዲሁም ወደ ሌሎች አገር ውስጥ የሚገኙ ኢዱስትሪ ፓርኮች እየፈለሱ መሆናቸውን አክለዋል፡፡
7.1K views14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 00:01:51
ማንችስተር ሲቲ ድል ቀንቶታል

ተጠባቂ በነበረው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ አርሰናልን በሜዳው ያስተናገደው ማንቸስተር ሲቲ 4ለ1 በማሸነፍ ሙሉ 3 ነጥብ ይዞ መውጣት ችሏል።
1.8K views21:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 18:27:17
ዓየር መንገዱ በ4 ዘርፎች የዓመታዊው ዓለም አቀፍ የጉዞ ሽልማት ዕጩ ሆነ።

የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ የዓመታዊው ዓለም አቀፍ የጉዞ ሽልማት (ወርልድ ትራቭል አዋርድ) በአራት ዘርፎች ዕጩ ሆኖ መቅረቡን ገልፆ በማህበራዊ ትስስር ገፁ በተቀመጡት ሊንኮች ኢትዮጵያዊያን ድምፅ እንዲሰጡትም ጠይቋል፡፡

ዓየር መንገዱ ÷ “ምርጥ የ2023 የአፍሪካ ዓየር መንገድ” ፣ “ምርጥ የ2023 የአፍሪካ ዓየር መንገዶች የንግድ ምልክት”፣ “ምርጥ የ2023 የአፍሪካ ዓየር መንገዶች ቢዝነስ ክላስ “ እና  በ “ምርጥ የ2023 የአፍሪካ ዓየር መንገዶች ኢኮኖሚ ክላስ ” ዓመታዊ ዓለም አቀፍ የሽልማት ዘርፎች ዕጩ መሆኑን የዓየር መንገዱ  መረጃ ያመላክታል፡፡
4.5K views15:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 17:35:09
በዲጂታል የክፍያ ዘዴ የተጀመረው የነዳጅ ግብይት ለነዳጅ እጥረት መፈጠር ምክንያት እንዳይሆን ስጋት ጥሏል ተባለ።

አዲሱን አሠራር ከመተግበር ጋር በተያያዘ፣ ተገልጋዮች ከመጠን በላይ የነዳጅ ግዥ እየፈጸሙ በመሆኑ፣ በአንዳንድ ማደያዎች የነዳጅ እጥረት እየተፈጠረ መሆኑ ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

የዲጂታል ክፍያ መተግበሪያውን ለመጠቀም የተፈጠረው ብዥታ በብዙ ማደያዎች ረዣዥም ሠልፎች እንዲታዩ ከማድረጉም በላይ፣ ቶሎ ነዳጅ ቀድቶ ለመሄድ አዳጋች እንዲሆን አድርጎታል ነው የተባለው፡፡

የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማኅበር በበኩሉ፣ አሁን ያለው መጨናነቅ የተፈጠረው አገልግሎቱን ለማስጀመር በቂ ጊዜ ባለመሰጠቱና አሽከርካሪዎች አገልግሎቱ ከመጀመሩ በፊት እንዲዘጋጁ ባለመደረጉ ነው ብሏል፡፡
4.8K views14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 16:06:41
የአለም የቡና ምርት ቅናሽ የታየበት ቢሆንም የኢትዮጵያ ምርት ጭማሪ ማሳየቱን የአለምአቀፉ የቡና ድርጅት አስታወቀ፡፡

ድርጅቱ ባወጣው አመታዊ ሪፖርት ይፋ እንዳደረገው ባሳለፍነው አመት የቡና ምርት ዘመን የአለም የቡና ምርት በ1.4 በመቶ ቅናሽ ታይቶበታል፡፡

ሆኖም የቡና መገኛ በሆነችው ኢትዮጵያ ምርቱ በ 2014 የምርት ዘመን የ3.6 በመቶ የምርት ጭማሪ መመዝገቡን አመታዊው ሪፖርት ያሳያል፡፡

ለእድገቱ እንደምክንያት የተጠቀሰው በዘርፉ አገሪቱ ተግባራዊ እያደረገች የምትገኘው የተለያዩ ስራዎች ናቸው መባሉን ካፒታል ዘግቧል።
5.0K views13:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 13:35:09
ሳፋሪኮም 743.6 ሚሊዮን ብር ክፍያ መፈጸሙ ተሰማ

በኢትዮጵያ ለሚሰማሩ የውጭ የቴሌኮም መሠረተ ልማት አልሚዎች የቴሌኮም መሠረተ ልማትን ከሀገር ውስጥ ኦፕሬተሮች የመከራየት አስገዳጅ አሠራር ተግባራዊ መደረጉ ይታወሳል። ይኽም የኢትዮ ቴሌኮም የገበያ አቅምን ፈጥሯል። 

በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የውጭ የግል የቴሌኮም አገልግሎት ፈቃድ ያገኘው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዚሁ አስገዳጅ ሕግ መሠረት የራሱን የቴሌኮም መሠረተ ልማት መገንባት ስለማይችል የኢትዮ ቴሌኮምን መሠረተ ልማት በኪራይ የመጠቀም ግዴታ ውስጥ ገብቷል።

በዚህም መሠረት ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የኢትዮ ቴሌኮምን መሠረተ ልማት መጠቀም የጀመረ ሲሆን፣ በ2015 ዓ.ም. የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውስጥም ከኢትዮ ቴሌኮም ለሚያገኘው የመሠረተ ልማት መጋራት አገልግሎት 743.6 ሚሊዮን ብር ክፍያ መፈፀሙን ሪፖርተር አስነብቧል።
5.6K views10:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 13:30:25
ኢትዮጵያ የሴካፋ ውድድር እንድታዘጋጅ ተመረጠች

ሴካፋ ከሚያከናውናቸው ውድድሮች አንዱ የሆነው የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ወንዶች የ2023 ውድድር በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በሐምሌ ወር መጨረሻ አዲስ አበባ ላይ እንደሚካሄድ ተረጋግጧል።

ይህ ውድድር ከሁለት ዓመት በፊት በ2013 ሲካሄድ ኢትዮጵያ ባህር ዳር ስታዲየም ላይ ማዘጋጀቷ የሚታወስ ነው።
5.2K views10:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 13:10:40
በሳተላይት ቴሌኮም ዘርፍ ስመጥር የሆነው ኩባንያ ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ፈቃድ ጠየቀ

መቀመጫውን ለንደን ያደረገው የሳተላይት ቴሌኮም አገልግሎት ዘርፍ ስመጥር የሆነው አቫንቲ ኮሙዩኒኬሽን ወደ ኢትዮጵያ የመግባት ዓላማ እንዳለውና የአገሪቱን የኢንተርኔት ግንኙነት ማሳደግ እንደሚፈልግ የአቫንቲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ካይል ዋይትሂል ለውጭ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል ሲል ሪፖርተር ዘግቧል።

ኩባንያው ይህንን ዕቅድ ለማሳካትም የቴሌኮም የሥራ ፍቃድ ከኢትዮጵያ መንግሥት እንደጠየቀ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ጠቁመዋል። በተጨማሪም በኢትዮጵያ ከሚገኙ የቴሌኮም ተቋማት ጋር አጋርነትን ለመፍጠር ኩባንያው ፍላጎት እንዳለው የገጹት ኃላፊው፣ በዚህም ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያና ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ውይይት መጀመሩን ዋይትሂል ለመገናኛ ብዙኃን ተናግሯል።

በተጨማሪም አቫንቲ በምሥራቅ አፍሪካ ለሚካሄደው መስፋፋት ሶማሊያን ቀጣዩ መዳረሻው የማድረግ ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል። አቫንቲ ባለፈው መስከረም ወር ተመሳሳይ ስምምነት ከቱርክ ቴሌኮም ኩባንያ ቱርክ ሳት (TurkSat) ጋር ማድረጉ ታውቋል።
5.2K views10:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ