Get Mystery Box with random crypto!

ዓየር መንገዱ በ4 ዘርፎች የዓመታዊው ዓለም አቀፍ የጉዞ ሽልማት ዕጩ ሆነ። የኢትዮጵያ ዓየር መ | ሰሌዳ | Seleda

ዓየር መንገዱ በ4 ዘርፎች የዓመታዊው ዓለም አቀፍ የጉዞ ሽልማት ዕጩ ሆነ።

የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ የዓመታዊው ዓለም አቀፍ የጉዞ ሽልማት (ወርልድ ትራቭል አዋርድ) በአራት ዘርፎች ዕጩ ሆኖ መቅረቡን ገልፆ በማህበራዊ ትስስር ገፁ በተቀመጡት ሊንኮች ኢትዮጵያዊያን ድምፅ እንዲሰጡትም ጠይቋል፡፡

ዓየር መንገዱ ÷ “ምርጥ የ2023 የአፍሪካ ዓየር መንገድ” ፣ “ምርጥ የ2023 የአፍሪካ ዓየር መንገዶች የንግድ ምልክት”፣ “ምርጥ የ2023 የአፍሪካ ዓየር መንገዶች ቢዝነስ ክላስ “ እና  በ “ምርጥ የ2023 የአፍሪካ ዓየር መንገዶች ኢኮኖሚ ክላስ ” ዓመታዊ ዓለም አቀፍ የሽልማት ዘርፎች ዕጩ መሆኑን የዓየር መንገዱ  መረጃ ያመላክታል፡፡