Get Mystery Box with random crypto!

ሰሌዳ | Seleda

የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የሰርጥ አድራሻ: @seledadotio
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.39K
የሰርጥ መግለጫ

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@seleda_support ለማንኛውም አይነት ጥያቄ

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 12

2023-05-12 09:04:54
አንጋፋዋ ድምጻዊት ሂሩት በቀለ አረፈች፡፡

ሕይወት እንደሸክላን ጨምሮ በርካታ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎችን እንካችሁ ያለችው ድምጻዊት ሂሩት በቀለ፣ በአደረባት ህመም በሃገር ውስጥና በውጭ በህክምና ስትረዳ ቆይታ በዛሬው እለት ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም በ80 ዓመቷ ህልፈተ-ሕይወቷ ተሰምቷል፡፡

ከ1950 መጀመሪያ እስከ 1980ዎቹ መጨረሻ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎችን ያስደመጠችን ሂሩት በቀለ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዘማሪነት/አገልጋይነት ስራዎችን ስትስራ እንደነበር ይታወሳል፡፡
6.3K views06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 08:37:18
ጠቅላይ ሚንስትሩ የሚያስገነዝቡት አዲሱ ቤተመንግሥት ወጪው 850 ቢሊዮን ብር ሊደርስ ይችላል ተባለ።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የሚያስገነቡት አዲሱ ቤተመንግሥት አጠቃላይ ወጪው 49 ቢሊዮን ብር እንደሚደርስ ሲገለጽ የቆየ ቢሆንም፣ የምዕራባዊያን ዲፕሎማቲክ ምንጮች ግን ወጪው 850 ቢሊዮን ብር ሊደርስ እንደሚችል በመናገር ላይ መሆናቸውን ዋዜማ ዘግባለች።

ለአዲሱ ቤተመንግሥት ተጨማሪ ሦስት ተቋራጮች መቅጠራቸውንም ዘገባው አክሏል። የጫካው ፕሮጀክት በ503 ሔክታር ላይ የቅንጡ መኖሪያ፤ መዝናኛ መንደሮችንና ሦስት ሰው ሠራሽ ሐይቆች ግንባታ ያካተተ ሲኾን፣ ግንባታው የሚካሄደው በየካ ክፍለ ከተማ የካ ተራራ ግርጌ ነው። የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን እስካኹን የ29 ኪሎ ሜትር የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ አካሂዷል።

ምንጭ - ዋዜማ
6.4K views05:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 18:14:25
ዜና ድሮ ቀረ...  አይ ፋንቱ

ፋንቱ ያለሰፈሯ ሌሊት ስትዞር ተይዛ ታሰረች

ወይዘሮ ፋንቱ ወልደማሪያም የተባለች በንፋስ ስልክ አካባቢ የምትኖር ሴት ያለሰፈሯ ከምሽቱ በ10 ሰዓት በየካቲት 12 አደባባይ ስትዘዋወር በመገኘቷ ተይዛ የሶስተኛ ወረዳ ፍርድ ቤት የአንድ ወር እስራት የቀጣት መሆኑን አስታውቋል፡፡

ወይዘሮ ፋንቱ ስትዘዋወር መገኘቷንና ተላላፊ መኪናዎችንም አድርሱኝ በማለት ማስቸገሯን ፖሊሶች መመስከራቸው ታውቋል፡፡

ተከሳሿም ፍርድ ቤት ቀርባ በተጠየቀች ጊዜ በአድራጎቷ ጥፋተኛ መሆኗን ስላመነች፤ ፍርዱ ተሸሽሎላት በ30 ብር መቀጫ ወይም በአንድ ወር እስራት እንድትቀጣ ተደርጎ መቀጫውን መክፈል ስላልቻለች አንድ ወር እንድትታሰር ወደ ወህኒ ወርዳለች ሲል ከአንደኛ ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ ከሶስተኛ ወረዳ ፍርድ ቤት የተገኘ ዜና ያስረዳል፡፡

ጥቅምት 7 ቀን 1963 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመ
7.4K views15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 15:56:27
በኢንዱስትሪ ፓርክና የአበባ እርሻዎች ውስጥ የሚሰሩት ሴቶች በሚያገኙት ገቢ የእለት ጉርሳቸውን ማሟላት ስላልቻሉ አጠቃላይ ደህንነታቸው አደጋ ላይ መሆኑን አንድ ጥናት አመላከተ

ስሪዊ የተሰኘው ተቋም አጠናሁት ባለው መረጃ መሰረት ከ67 በመቶ በላይ የሚሆኑ ተቀጣሪ ሴቶች ደሞዛቸው የእለት ጉርሳቸውን አያሟላም።

ሴቶቹ በስራቸው ልክ ክፍያ ባለማግኘታቸው ምሳቸውን እንኳ እንደሚዘሉ፤ ለኪራይ የሚቀንስ ቤት ተከራይተው ረጅም ርቀት እንደሚጓዙ የተነገረ ሲሆን ይህም በሴቶቹ ላይ የአካልም የአእምሮም ጉዳት አድርሶባቸውል ብሏል።

በብዙዎቹ ኢንዱስትሪዎች ደግሞ የህጻናት ማቆያ ባለመኖሩ ልጅ ከወለዱ በኋላም ወደ ስራ የማይመለሱት ቁጥራቸው ከፍተኛ ነው ተብሏል።

እንደ መፍትሄም ድርጅቶች የሰራተኞቻቸውን የመጠለያ የትራንስፖርት ችግር ቢፈቱ፤ ምግብ ቢያቀርቡ፤ በነጻ የሚጠቀሙበት የህጻናት ማቆያ በማዘጋጀት ችግራቸውን ማቃለል ይቻላል ተብሏል።
7.2K views12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 14:58:12
በመዲናዋ ሲሚንቶ ከታሪፍ በላይ ሲሸጡ የተገኙ 89 የንግድ ሱቆች ታሸጉ

የከተማ አስተዳደሩ ንግድ ቢሮ መንግሥት ያወጣው የሲሚንቶ የማከፋፈያና የችርቻሮ ተመን ዋጋ እንዲከበር እንደሚሰራ ገልጾ፤ የተሰጡ ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያዎችን በተላለፋ 89 የንግድ ሱቆች ላይ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል።

እርምጃው የተወሰደባቸው በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና በለሚኩራ ክፍለ ከተማ የሚገኙና አለአግባብ ከተተመነው የሲሚንቶ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በላይ በመሸጥ፣ ምርት በመደበቅ መሸጫ ቦታቸውን ዘግተው በመጥፋት የተገኙ ሲሚንቶ አከፋፋዮችና ቸርቻሪዎች መሆናቸውን ቢሮው አስታውቋል።
7.0K views11:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 13:53:23
አዋሽ ባንክ በምርጥ ባንኮች ዝርዝር ውስጥ ከኢትዮጵያ ብቸኛው ባንክ ሆኖ ለሁለተኛ ጊዜ ተመረጠ።

አለም አቀፉ የፋይናንስ መፅሔት የዘንድሮ ዓመት ምረጥ ባንኮችን ዝርዝር ይፋ ሲያደርግ በአፍሪካ ምርጥ ባንኮች ዝርዝር ውስጥ ብቸኛው የኢትዮጵያ ተወካይ ሆኖ አዋሽ ባንክ ለሁለተኛ ጊዜ ተመርጧል።

በምርጫው ከአፍሪካ አህጉረ 36 ባንኮች ምርጦች ተብለው በግሎባል ፋይናንስ መፅሔት የተካተቱ ሲሆን መፅሔቱ ባንኮቹን መዝኖ ምርጥ ያላቸው በዋነኝነት የትርፍ እድገታቸውን ለደንበኞች ያለቸው ቅን አገልግሎትና ጠቅላላ ሀብታቸውን መርምሮ ነው ተባሏል፡፡

አዋሽ ባንከ ጠቅላላ ሀብቱ 3.9 ቢሊዮን ዶላር እንደደረሰ ግሎባል ፋይናንስ መፅሔት ጠቅሷል፡፡ አዋሽ ባንክ በመጪው ጥቅምት ወር በሞሮኮ ማራካሽ በሚካሄደው የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም(IMF) እና የአለም ባንክ የጋራ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ እውቅና ይሰጣቸዋል ተብሏል።
6.7K views10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 13:27:12
#የሰሌዳ_እለታዊ_የስራና_የጨረታ_ጥቆማ

የስራ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ አካል ድጋፍ አገልግሎት

የህዝብ ግንኙነትና ኮምኒኬሽን ባለሙያ
ኦውድዮ ቪዥዋል ቴክኒሻን ይፈልጋል
በያጅ፤ የብረታ ብረት ቴክኒሻን ይፈልጋል

አመልካቾች በዋናው መስሪያቤት ብርጭቆ ኮንዶሚኒየም በመገኘት መወዳደር ትችላላችሁ

የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት

የጠረቤዛ ቀን መቁጠሪያ በብዛት መግዛት እንደሚፈልግ አሳውቋል

ተጫራቾች የማይመልስ 300 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ትችላላችሁ
ተጨማሪውን መረጃ 0115512400 ማግኘት ትችላላችሁ

መልካም እድል
6.3K views10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 12:10:47
በፔሩ ከ200 በላይ ቀኝ እግር ጫማዎችን የሰረቁት ተጠርጣሪዎች እየተፈለጉ ነው

በደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር ፔሩ የተፈጸመው የዝርፊያ ወንጀል የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስቧል።

ሶስት ዘራፊዎች በማዕከላዊ ፔሩ ሁዋንካዮ ግዛት ጀኒን ከተማ የሚገኝ የስፖርት አልባሳት እና ጫማዎች መደብርን ሰብረው ይገባሉ።

በጥድፊያ ላይ የነበሩት ዘራፊዎች በካርቶን ታሽገው የተቀመጡ 220 የተለያዩ ብራንድ ጫማዎችን ሰብስበው ይዘው ይሰወራሉ።

አስገራሚው ዜና ግን ዘራፊዎቹ ሰብረው ከገቡት መደብር ይዘው የወጡት ሁሉም የቀኝ እግር ጫማ የመሆናቸው ጉዳይ ነው።

የመደብሩ ባለቤት የቀኝ እግር ጫማዎቹ ካልተገኙ የግራ እግሮቹን ጫማዎች በተናጠል መሸጥ ስለማልችል የ13 ሺህ ዶላር ኪሳራ ይደርስብኛል ብሏል።
6.4K views09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 10:40:41
አሜሪካ የታገዱ የሩሲያ ንብረቶችን ለዩክሬን ተላልፈው እንዲጡ መወሰኗ ተሰማ

የአሜሪከ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የታገዱ የሩሲያ ንብረቶች ለዩክሬን እንዲሰጡ የመጀመሪያ ውሳኔ ማሳለፉን አል-ዐይን ዘግቧል።

ለዩክሬን ተላለፎ የሚሰጠው ገንዘብም ከሩሲያዊው ባለሀብት ኮስታሊን ማሎፌቭ የተወረሰ እንደሆነም ጠቅላይ አቃቤ ህጉ አስታውቀዋል።

ከስድስት ሺህ በላይ ማዕቀቦች በአሜሪካ የተጣለባት ሩሲያ በበኩሏ ንብረቶቿን ለዩክሬን አሳልፎ መስጠት ሌላ መዘዝ ያስከትላል በማለት ማስጠንቀቋ ይታወሳል
6.5K views07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 09:52:19
ብርሃን ባንክ ለዋና መሥሪያቤቱ ህንጻ ያሸነፈውን ዲዛይን ይፋ አደረገ

ብርሃን ባንክ ለዋና መሥሪያቤቱ ህንፃ ግንባታ ዲዛይን ለማሠራት ባወጣው ዓለም አቀፍ ጨረታ አሸናፊ ሆኖ የተመሰጠውን ዲዛይን ይፋ አደረገ።

ባንኩ ባወጣው ዓለም አቀፍ ጨረታ ላይ 16 ኩባንያዎች የተሳተፉ ሲሆን ተሳታፊዎቹ ካቀረቧቸው ዲዛይኖች መካከል አሸናፊ የሆነው ዲዛይን ግንቦት 2 ቀን 2015 ዓ.ም. ምሽት በተካሄደ ፕሮግራም ላይ ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሠረት ባንኩ በሰንጋ ተራ አካባቢ በተረከበው 5400 ካሬ ሜትር መሬት ላይ ለሚያስገነባው ህንፃ MAE ኮንሰልቲንግ ኤንድ ኢንጂነርስ በተባለው ድርጅት የቀረበው ዲዛይን አሸናፊ ሆኖ ተመርጧል። በተመረጠው ዲዛይን መሠረት የሚገነባው የባንኩ ዋና መሥሪያቤት ህንፃ ከ 51 በላይ ወለሎች እንደሚኖሩት ታውቋል።
6.5K views06:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ