Get Mystery Box with random crypto!

ሰሌዳ | Seleda

የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የሰርጥ አድራሻ: @seledadotio
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.39K
የሰርጥ መግለጫ

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@seleda_support ለማንኛውም አይነት ጥያቄ

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2023-05-17 10:54:24
የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በከተማው ያለውን የነዳጅ እጥረት ለመቅረፍ ለ6 ባለሀብቶች የነዳጅ ማደያዎችን ለመገንባት የሚያስችላቸውን የሳይት ርክክብ ማድረጉን አስታወቀ።

የከተማው ከንቲባ ሙሀመድ አሚን በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው እንደገለጹት፥ ለዚሁ ሥራ 60 ባለሀብቶች ጥያቄ አቅርበው እንደነበር አንስተው ከዚህ ውስጥ መስፈርቱን አሟልተዋል የተባሉ 6 ባለሀብቶች ዝርዝር ወደ ክልል ተልኮ የተፈቀደላቸው መሆኑን ገልጸዋል።

በኮምቦልቻ ከተማ አሁን ላይ 8 ማደያዎች ሲኖሩ የ6ቱ ግንባታ ሲጠናቀቅ ቁጥሩ ወደ 14 ከፍ ይላል። ይኽም በከተማውና ዙሪያ አካባቢዎች የሚገጥመውን የነዳጅ እጥረት ይቀርፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከንቲባው ገልጸዋል።
6.8K views07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 09:03:08
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አትላንታ የሚያደርገውን አዲስ በረራ ጀመረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አሜሪካ አትላንታ የሚያደርገውን አዲስ በረራ ዛሬ መጀመሩን አስታውቋል። የበረራው ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በስካይላይት ሆቴል ተካሂዷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አትላንታ ዛሬ የሚጀምረው በረራ በአሜሪካ ያሉትን መዳረሻዎች ቁጥር ወደ ስድስት ያሳድገዋል።
6.9K views06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 07:54:10
አቡበከር ናስር ሻምፒዮን ሆኗል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የማሜሎዲ ሰንዳውንስ የፊት መስመር አጥቂ አቡበከር ናስር የመጀመሪያ የደቡብ አፍሪካ ሊግ ዋንጫውን በትላንትናው ዕለት አንስቷል።

የመጀመሪያው የውድድር ዓመቱን በሰንዳውንስ እያሳለፈ የሚገኘው አቡበከር ናስር በወሳኝ እና ትልልቅ ጨዋታዎች ላይ ግብ በማስቆጠር ቁልፍ ሚናን በአመቱ ተጫውቶ አሳልፏል።
7.0K views04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 20:00:33
አፍሪካዊቷ ሀገር ቱኒዚያ ለእግርኳስ ደጋፊዎች ልትከፍል ነው

የቱኒዚያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (FTF) በስታዲየሞች ውስጥ የሚደርሰውን ሁከትና ብጥብጥ ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት "የጥሩ ምግባር አርዓያ" ለሚሆኑ ደጋፊዎች የገንዘብ ሽልማት ሊያበረክት መሆኑን ተገልጿል።

በሀገሪቱ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተከሰቱ ግጭቶች ምክንያት የፖሊስ አባላት ቆስለዋል ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሰዎችም ታስረዋል።

ፌዴሬሽኑ በቱኒዚያ እግር ኳስ ሊግ በመታገዝ ደጋፊዎቹ “የጥሩ ምግባር አርዓያ” ናቸው ተብሎ ለሚታሰበው ቡድን በዚህ የውድድር ዘመን በቀሪው ጊዜ 10,000 ዲናር (£2,592 ፓውንድ) ለመስጠት አስቧል።
3.4K views17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 19:16:09
#ዘይገረም

የዩቲዩብ ተመልካች ለማግኘት ሲል ሆን ብሎ አውሮፕን እንዲከሰከስ ያደረገው አሜሪካዊ

ብዙ ተመልካች ለማግኘት ሲል ሆን ብሎ አውሮፕላን ወድቆ እንዲከሰከስ ያደረገው ዩቲዩበር ምርመራ በማደናቀፍ ጥፋተኛ መሆኑን ለማመን መስማማቱን የአሜሪካ ዐቃቤ ሕግ አሳውቋል።

ግለሰቡ አደጋው እንዲከሰት ካደረገ በኋላ የመንግሥት ባለሥልጣናት የአደጋውን ምክንያት እንዳይመረምሩ ለማድረግ ማስረጃዎችን አውሮፕላኑ ከወደቀበት ስፍራ ማጥፋቱም ተገልጿል።

ቴሬቨር ጃኮብ የተባለው የ29 ዓመት ግለሰብ አውሮፕላኑ በአደጋ የወደቀ በማስመሰል የቀረጸውን ቪዲዮ ከሁለት ዓመት በፊት ዩቲዩብ ላይ አቅርቦ እስካሁን ከ2.9 ሚሊዮን በላይ ዕይታን አግኝቷል።

ጥፋቱን ለማመን ከዐቃቤ ሕግ ጋር በደረሰው ስምምነት መሠረት ግለሰቡ ቪዲዮውን የቀረጸው አንድ ምርትን ለማስተዋወቅ በደረሰው ስምምነት መሆኑን አመልክቷል።

ግለሰቡ በድርጊቱ አስከ 20 ዓመታት የሚደርስ እስር ሊጠብቀው ይችላል መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል።
4.1K views16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 17:38:31
ወደ እርስ በርስ ጦርነት በገባችው ሱዳን የወጪና ገቢ ምርቶች ዋጋ በ60 በመቶ ማሻቀቡ ተሰማ

በተለይ እንደ ምግብና ነዳጅ ባሉት ገቢ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪው ማየሉን አፍሪካ ኒውስ ጽፏል። ሱዳን እንደ ሙጫ፤ ወርቅ፤ ሰሊጥና የቁም እንስሳትን ለውጪ ገበያ በማቅረብ ትታወቃለች።
4.7K views14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 14:03:13
የአዲስ አበባ ከተማ መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚሰጡበትን ጊዜ፤ ወደ 16 ሰዓት ለማራዘም የሚያስችል ጥናት እየተደረገ ነው ተባለ።

ጥናቱ የመስሪያ ቤቶቹን የስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 አስቀድሞ ለማስጀመር እና ከ11፡30 በኋላ እስከ ምሽት ለማስቀጠል ያቀደ ነው መባሉን ኢትዮጵያን ኢንሳይደር ዘግቧል።

ይህም “በአንዳንድ ተቋማት ላይ ከሰዓት ጋር ተይይዞ ተገልጋዮች ተገፍተው የሚወጡበትን” ሁኔታ ለማስቀረት ያለመ ነው ተብሏል።
5.9K views11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 12:30:08
ኤርሊንግ ሀላንድ የአመቱ ምርጥ እግር ኳስ ተጫዋች ተባለ

ኖርዌያዊው የማንችስተር ሲቲ የፊት መስመር ተጫዋች የውድድር ዓመቱ የእግር ኳስ ፀሀፊዎች የአመቱ ምርጥ ተጫዋች በመባል መመረጡ ይፋ ተደርጓል።

82% ድምፆችን መሰብሰብ የቻለውን ኤርሊንግ ሀላንድን በመከተል ቡካዮ ሳካ፤ ማርቲን ኦዴጋርድና ኬቨን ዴብሮይን ተከታዮቹን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።
6.0K views09:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 12:23:39
አነጋጋሪው ባለሃብት ኢለን መስክ አዲስ የትዊተር ስራ አስፈጻሚ በመቅጠር እራሱን ለሌላ ሹመት አጨ።

የአለማችን ቱጃሩ ሰው ኢለን መስክ እስካሁን ስማቸው ያልተጠቀሱ ሴት ስራ አስፈጻሚ በሱ ቦታ ሆነው በስድስት ሳምንታት ውስጥ ማህበራዊ የትስስር ገጹን እንደሚረከቡ ተናግሯል።

ቢሊየነሩ በትዊተር ገጻቸው ውሳኔውን ያበሰሩ ሲሆን፤ "የእኔ ሚና ወደ ኤክሴክ ሊቀመንበር እና የቴክኖሎጂ ዋና ኃላፊ በመሆን ምርትንና ሶፍትዌሮችን ወደ መቆጣጠር ይሸጋገራል" ብለዋል።
5.8K views09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 11:47:36
የህንድ አንዲት ግዛት ከልክ በላይ ውፍረት ያለባቸውን ፖሊሶች ከስራ ልታግድ ነው

በህንድ ግዛት በሆነችው አሳም የአልኮል መጠጥ ሱሰኛ የሆኑ እንዲሁም ከልክ በላይ ውፍረት ያለባቸው የፖሊስ አባላት ከስራቸው ሊሰናበቱ ነው መባሉ ተሰምቷል።
 
የግዛቲቱ ባለስልጣናት እንዳሉት ከላይ በተገለፁት ምክንያቶች ሳቢያ ከ300 በላይ የፖሊስ መኮንኖች ስራቸውን በራሳቸው ፍቃድ እንዲለቁ እየተጠየቁ ነው። በአለም ጤና ድርጅት መረጃ መሠረት 11 በመቶ ህንዳውያን ጠጪዎች መሆናቸው ይነገራል።
5.9K views08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ