Get Mystery Box with random crypto!

#ዘይገረም የዩቲዩብ ተመልካች ለማግኘት ሲል ሆን ብሎ አውሮፕን እንዲከሰከስ ያደረገው አሜሪካዊ | ሰሌዳ | Seleda

#ዘይገረም

የዩቲዩብ ተመልካች ለማግኘት ሲል ሆን ብሎ አውሮፕን እንዲከሰከስ ያደረገው አሜሪካዊ

ብዙ ተመልካች ለማግኘት ሲል ሆን ብሎ አውሮፕላን ወድቆ እንዲከሰከስ ያደረገው ዩቲዩበር ምርመራ በማደናቀፍ ጥፋተኛ መሆኑን ለማመን መስማማቱን የአሜሪካ ዐቃቤ ሕግ አሳውቋል።

ግለሰቡ አደጋው እንዲከሰት ካደረገ በኋላ የመንግሥት ባለሥልጣናት የአደጋውን ምክንያት እንዳይመረምሩ ለማድረግ ማስረጃዎችን አውሮፕላኑ ከወደቀበት ስፍራ ማጥፋቱም ተገልጿል።

ቴሬቨር ጃኮብ የተባለው የ29 ዓመት ግለሰብ አውሮፕላኑ በአደጋ የወደቀ በማስመሰል የቀረጸውን ቪዲዮ ከሁለት ዓመት በፊት ዩቲዩብ ላይ አቅርቦ እስካሁን ከ2.9 ሚሊዮን በላይ ዕይታን አግኝቷል።

ጥፋቱን ለማመን ከዐቃቤ ሕግ ጋር በደረሰው ስምምነት መሠረት ግለሰቡ ቪዲዮውን የቀረጸው አንድ ምርትን ለማስተዋወቅ በደረሰው ስምምነት መሆኑን አመልክቷል።

ግለሰቡ በድርጊቱ አስከ 20 ዓመታት የሚደርስ እስር ሊጠብቀው ይችላል መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል።