Get Mystery Box with random crypto!

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በከተማው ያለውን የነዳጅ እጥረት ለመቅረፍ ለ6 ባለሀብቶች የነዳጅ ማደ | ሰሌዳ | Seleda

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በከተማው ያለውን የነዳጅ እጥረት ለመቅረፍ ለ6 ባለሀብቶች የነዳጅ ማደያዎችን ለመገንባት የሚያስችላቸውን የሳይት ርክክብ ማድረጉን አስታወቀ።

የከተማው ከንቲባ ሙሀመድ አሚን በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው እንደገለጹት፥ ለዚሁ ሥራ 60 ባለሀብቶች ጥያቄ አቅርበው እንደነበር አንስተው ከዚህ ውስጥ መስፈርቱን አሟልተዋል የተባሉ 6 ባለሀብቶች ዝርዝር ወደ ክልል ተልኮ የተፈቀደላቸው መሆኑን ገልጸዋል።

በኮምቦልቻ ከተማ አሁን ላይ 8 ማደያዎች ሲኖሩ የ6ቱ ግንባታ ሲጠናቀቅ ቁጥሩ ወደ 14 ከፍ ይላል። ይኽም በከተማውና ዙሪያ አካባቢዎች የሚገጥመውን የነዳጅ እጥረት ይቀርፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከንቲባው ገልጸዋል።