Get Mystery Box with random crypto!

ሰሌዳ | Seleda

የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የሰርጥ አድራሻ: @seledadotio
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.47K
የሰርጥ መግለጫ

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@seleda_support ለማንኛውም አይነት ጥያቄ

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-05-20 19:16:38
በ“ሿሿ” የስርቆት ወንጀል ከሚያገኙት ገንዘብ በቀን እስከ 35 ሺህ ብር ሲቆጥቡ ነበር የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በተሽከርካሪ ታግዘው የሞባይል ስልክ ስርቆት ወንጀል በመፈፀም የተጠረጠሩ 25 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ከተጠርጣሪዎቹ 6ቱ ሴቶች ሲሆኑ ግለሰቦቹ “ሿሿ” ብለው በሚጠሩት ወንጀል ከሚያገኙት ገንዘብ በቀን እስከ 35 ሺህ ብር እንደሚቆጥቡ በምርምራ ደርሼበታለሁ ብሏል የአዲስ አበባ ፖሊስ።

ከተጠርጣሪዎቹ እጅ ሁለት ሚኒባስ ታክሲዎች እንዲሁም ለወንጀል ሥራቸው የሚጠቀሙባቸውን 4 ተጨማሪ ተሽከርካሪዎችን መያዙን ፖሊስ ገልጿል። በተጨማሪም 14 ዘመናዊ ሞባይል ስልኮች እና ገንዘብ ስለመገኘቱም የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያስረዳል።
7.5K viewsedited  16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 16:13:42
ኤክሳይዝ ታክስ ማን ይከፍላል?

ኤክሳይዝ ታክስ በተወሰኑ የምርት እና የአገልግሎት ባህሪ ባላቸው ቁሳቁሶች እና አገልግሎቶች ላይ በዋናነት በአምራቾች እና አስመጪዎች ላይ የሚጣል ቀጥተኛ ያልሆነ የታክስ አይነት ቢሆንም እንደአለመታደል ሆኖ ከዋጋ ጋር ለሸማች አውርደው ይሰጡታል!

ጥያቄው ነባር ኤክሳይዝ ታክስ ሲቀነስ ከነባር ዋጋ መውረድ ያለመደው ገበያ (ገደብ የሌለው የትርፍ ጣሪያ ጭማሪ ፍላጎት) ባለበት የሸማች ጫና ይቀንሳል ወይ የሚለው ነው!

ታክስ ሊጨመርም ሊቀነስም ይችላል! ለምሳሌ ሀገራት ታክስ ለመጨመር ሲወስኑ የሚከተለው አመክንዮ ሊኖራቸው ይችላል ሊቀንሱ ሲያስቡም በተቃራኒው.....

መንግስታት በሁለት መንገድ ታክስን ሊጨምሩ ይችላሉ፤ አንደኛው የገቢ መጠናቸውን በመጨመር ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ለማዋል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የገንዘብ አቅርቦትን እና ፍላጎትን ለመቆጣጠር በሚያስቡበት ወቅት ነው፤ #ለምሳሌ የገንዘብ አቅርቦት በሰዎች እጅ ሲበዛ በታክስ ሰበብ መሰብሰብ የተለመደ አሰራር ነው፤ የገንዘብ አቅርቦትን ለመጨመር ታክስ መቀነስ ሌላው አሰራር ነው (ታክስ ተቀነሰ ማለት ሰዎች ለመንግስት ይከፍሉት የነበረው ገንዘብ እጃቸው ላይ ይቆያል ማለት ነው)።

በተጨማሪም ከውጪ በሚገቡ ቁሳቁሶች ላይ የሚጣል ታክስ የውጪ ምንዛሬን አቅርቦት መሰረት ያደረገ መሆን ስለሚኖርበት ሀገራት ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ  እጥረት ሲገጥማቸው ከውጪ በሚገቡ እና መሰረታዊ በማይባሉ ቁሶች ላይ ተጨማሪ ታክስ ይጥላሉ::

Via - The Ethiopian Economist View
7.3K views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 14:22:41
“ሳቅ የጠፋባቸው” ጃፓናዊያን ወደ ሳቅ ትምህርት ቤት ለመግበት ተገደዋል ተባለ

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለሶስት ዓመታት ማስክ ሲያደርጉ የነበሩ ጃፓናዊያን ሳቅ ጠፍቶባቸዋል። ይህን ተከትሎም የሳቅ ትምህርት ቤቶች ገበያው ደርቶላቸዋል ተብሏል።

መሳቅን የረሱ ከአራት ሺህ በላይ ዜጎችም እንደቀድሟቸው ፈገግ ለማለት ወደ ሳቅ ትምህርት ቤቶች ማቅናታቸውን ጃፓን ታየምስ ዘግቧል።
6.9K views11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 13:09:56
"የመኪና አስመጪዎች አዲስ ተሽከርካሪዎች ገበያ ላይ የሚሸጡበት ዋጋና ለገዥ የሚቆርጡት ደረሰኝ ሰፊ ልዩነት እንዳለው በጥናቴ አረጋግጫለሁ " - የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በተሽከርካሪዎች ግብይትና አሰራር ዙሪያ ትላንት በሰጠው መግለጫ የተሽከርካሪዎች ግብይት መሬት ላይ ያለው እውነታ መንግስት ማግኘት የሚገባውን ገቢ መሠረት ያላደረገ መሆኑን በጥናቴ ደርሼበታለሁ ብሏል።

በዚህም መነሻ ከአስመጪዎችና ከዘርፉ ተሳታፊዎች ጋር ውይይት መደረጉንና ማንም በገበያ ዋጋ ደረሰኝ እንዲቆርጥና ገዢውም ትክክለኛ ደረሰኝ በመያዝ አገልግሎት ማግኘት እንዳለበት የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አሳስቧል።

ግብር ለመቀነስ በሚል አዲስ ተሽከርካሪዎች ገበያ ላይ ከሚሸጡበት ዋጋ በተቃራኒ የሃሰት ዋጋ ዝቅ አርጎ ደረሰኝ መቁረጥ በህግ ስለሚያስጠይቅ ሻጮች ከዚህ ድርጊት እንዲቆጠቡ ቢሮው በአፅንኦት አሳስበዋል።
7.0K views10:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 12:46:19
አዩቴ ኢትዮጵያ አስር ሺህ የአሜሪካን ዶላር የሚያሸልም ውድድር ለስራ ፈጠሪ ወጣቶች ይፋ አደረገ

በአዩቴ ኢትዮጵያ ተዘጋጅቶ የቀረበው የግብርና ዘርፍ የስራ ፈጠራ የወጣቶች ውድድር የሰብል የአትክልትና ፍራፍሬ ዘርፎችን የሚያሳድግን አዳዲስ ሀሳቦችና የፈጠራ ስራ ያላቸው ወጣቶች ብቻ የሚስተናገዱበት ነው ተብሏል።

የማመልከቻ ጊዜው የሚቆየው ከግንቦት 7 እስከ ግንቦት 22 ብቻ ነው የተባለ ሲሆን ውድድሩን በአንደኝነት ለሚያሸንፈው ወጣት የአስር ሺህ የአሜሪካን ዶላር በድምሩ ለሶስት አሸናፊዎች የሀያ ሺህ የአሜሪካን ዶላር ጉርሻ መዘጋጀቱን ሰምተናል።

የማመልከቻ ሊንክ: https://ayute-ethiopia.et/apply-here/
ዌብሳይት: www.ayute-ethiopia.et
6.6K views09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 17:00:03
በፕርሜር ሊጉ ለኮከብ ጎል አግቢነት የሚፎካከረው አጥቂ ቤቲንግ በመጫወቱ ለስምንት ወራት ከስፖርት ታገደ

እንግሊዛዊዉ የብሬንትፎርዱ አጥቂ ኢቫን ቶኒ የኤፌውን ህግ በመተላለፍ በእግር ኳስ ጨዋታ ውርርድ በማድረጉ (ቤቲንግ በመጫወቱ) ለስምንት ወራት ከምንም አይነት የእግር ኳስ ውድድር እንዲገለል እና 50ሺ ዩሮ እንዲቀጣ ተወስኖበታል።

ወጣቱ ተስፈኛ በዘንድሮ የውድድር ዓመት ድንቅ አቋማቸውን ካሳዩ ጥቂት የሊጉ አጥቂዎች አንዱ ሲሆን በ20 የፕርሚዬር ሊግ ጎሎች ከሀላንድ እና ሀሪ ኬን በመቀጠል ሶስተኛው የሊጉ ኮከብ ግብ አግቢም ነበር።

የበርካታ አምራች ወጣቶችን አእምሮ በበረዘው የቤቲንግ ውድድር ሱስ ምክንያት ከዚህ ቀደም በሃገራችንም የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች ናትናኤል በርሄን የራሱ ክለብ ይሸነፋል ብሎ መጫወቱን ተከትሎ ከክለቡ መባረሩ አይዘነጋም።
4.3K views14:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 14:23:06
ዜጎችና ተወላጆች በሃዋላ ከውጪ በሚልኩት ገንዘብ ላይ የሚጠየቀው የአገልግሎት ክፍያ እንዲቀነስ ተጠየቀ

የኢጋድ አባል ሀገሮች የብሄራዊ ብንኮች ገዢዎች በኬንያ ናይሮቢ በነበራቸው ስብሰባ ላይ በቀረበ ጥናት በአባል ሃገራቱ ላይ የሚጠየቀው ያገልግሎት ክፍያ ከአለማቀፉ አማካኝ ክፍያ በእጅጉ የበለጠ ነው መባሉን ቢዝነስ ዴሊ ጽፏል።

ለኢጋድ አባል ሀገሮች የሚጠየቀው ክፍያ በአማካኝ 8.9 በመቶ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ አማካኙ 6.5 በመቶ እንደሆነ ተመላክቷል። ኢጋድም ይህ ያገልግሎት ክፍያ እንዲቀነስ ጠይቋል።
5.3K views11:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 14:05:02
#የሰሌዳ_እለታዊ_የስራና_የጨረታ_ጥቆማ

የስራ ማስታወቂያ

አዲስ ፋና ጠቅላላ ሸቀጥና ሆቴሎች ንግድ አክሲዮን ማህበር

ዋና ስራ አስኪያጅ

አመልካቾች ተጨማሪውን መረጃ 0111567003 በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ

መልካም እድል
5.3K views11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 13:36:31
በአዲስ አበባ አንድ እቁላል ከ14 ብር እስከ 16 ብር እየተሸጠ ነው ተባለ፡፡

በመኖ መወደድ እና ከዚህ ቀደም ተከስቶ በነበረው ወረርሺኝ ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶሮዎች መሞታቸው አብዛኛው ዶሮ አርቢ አባላትን ዘርፉ ውስጥ እንዳይቆዩ እያደረጋቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ዶሮ አርቢዎች እና አቀናባሪዎች ማህበር ገልኡአል፡፡

ማህበሩ የመኖው መወደድ የእንቁላል ዋጋ ከዚህም በላይ ከፍ እንዲል ሊያደርገው እንደሚችል ስጋቱን ገልጿል፡፡ አሁን ላይ በአማካይ የ1 እንቁላል ዋጋ ከ 14 ብር አስከ 16 ብር እየተሸጠ መሆኑን ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል።
5.4K views10:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 12:50:40
ታማኝነት

በኢትዮጵያ አየርመንገድን ለ32 አመት ያገለገሉት አቶ አማረ ታደሰ በቦሌ ኤርፖርት የቢዝነስ ክላስ ላውንጅ ባር ማን ናቸው።

ተረስቶ ያገኙትን የአንድ ናጄሪያዊ መንገደኛ 200,000 ዶላር ለባለቤቱ አስረክበዋል። ታማኝ ሰው ናቸው።

(ጋዜጠኛ  ቃለየሱስ በቀለ)
5.4K views09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ