Get Mystery Box with random crypto!

ዜጎችና ተወላጆች በሃዋላ ከውጪ በሚልኩት ገንዘብ ላይ የሚጠየቀው የአገልግሎት ክፍያ እንዲቀነስ ተጠ | ሰሌዳ | Seleda

ዜጎችና ተወላጆች በሃዋላ ከውጪ በሚልኩት ገንዘብ ላይ የሚጠየቀው የአገልግሎት ክፍያ እንዲቀነስ ተጠየቀ

የኢጋድ አባል ሀገሮች የብሄራዊ ብንኮች ገዢዎች በኬንያ ናይሮቢ በነበራቸው ስብሰባ ላይ በቀረበ ጥናት በአባል ሃገራቱ ላይ የሚጠየቀው ያገልግሎት ክፍያ ከአለማቀፉ አማካኝ ክፍያ በእጅጉ የበለጠ ነው መባሉን ቢዝነስ ዴሊ ጽፏል።

ለኢጋድ አባል ሀገሮች የሚጠየቀው ክፍያ በአማካኝ 8.9 በመቶ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ አማካኙ 6.5 በመቶ እንደሆነ ተመላክቷል። ኢጋድም ይህ ያገልግሎት ክፍያ እንዲቀነስ ጠይቋል።