በፕርሜር ሊጉ ለኮከብ ጎል አግቢነት የሚፎካከረው አጥቂ ቤቲንግ በመጫወቱ ለስምንት ወራት ከስፖርት ታገደ እንግሊዛዊዉ የብሬንትፎርዱ አጥቂ ኢቫን ቶኒ የኤፌውን ህግ በመተላለፍ በእግር ኳስ ጨዋታ ውርርድ በማድረጉ (ቤቲንግ በመጫወቱ) ለስምንት ወራት ከምንም አይነት የእግር ኳስ ውድድር እንዲገለል እና 50ሺ ዩሮ እንዲቀጣ ተወስኖበታል። ወጣቱ ተስፈኛ በዘንድሮ የውድድር ዓመት ድንቅ አቋማቸውን ካሳዩ ጥቂት የሊጉ አጥቂዎች አንዱ ሲሆን በ20 የፕርሚዬር ሊግ ጎሎች ከሀላንድ እና ሀሪ ኬን በመቀጠል ሶስተኛው የሊጉ ኮከብ ግብ አግቢም ነበር። የበርካታ አምራች ወጣቶችን አእምሮ በበረዘው የቤቲንግ ውድድር ሱስ ምክንያት ከዚህ ቀደም በሃገራችንም የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች ናትናኤል በርሄን የራሱ ክለብ ይሸነፋል ብሎ መጫወቱን ተከትሎ ከክለቡ መባረሩ አይዘነጋም። 4.3K views14:00