Get Mystery Box with random crypto!

በ“ሿሿ” የስርቆት ወንጀል ከሚያገኙት ገንዘብ በቀን እስከ 35 ሺህ ብር ሲቆጥቡ ነበር የተባሉ ግለ | ሰሌዳ | Seleda

በ“ሿሿ” የስርቆት ወንጀል ከሚያገኙት ገንዘብ በቀን እስከ 35 ሺህ ብር ሲቆጥቡ ነበር የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በተሽከርካሪ ታግዘው የሞባይል ስልክ ስርቆት ወንጀል በመፈፀም የተጠረጠሩ 25 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ከተጠርጣሪዎቹ 6ቱ ሴቶች ሲሆኑ ግለሰቦቹ “ሿሿ” ብለው በሚጠሩት ወንጀል ከሚያገኙት ገንዘብ በቀን እስከ 35 ሺህ ብር እንደሚቆጥቡ በምርምራ ደርሼበታለሁ ብሏል የአዲስ አበባ ፖሊስ።

ከተጠርጣሪዎቹ እጅ ሁለት ሚኒባስ ታክሲዎች እንዲሁም ለወንጀል ሥራቸው የሚጠቀሙባቸውን 4 ተጨማሪ ተሽከርካሪዎችን መያዙን ፖሊስ ገልጿል። በተጨማሪም 14 ዘመናዊ ሞባይል ስልኮች እና ገንዘብ ስለመገኘቱም የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያስረዳል።