Get Mystery Box with random crypto!

ኤክሳይዝ ታክስ ማን ይከፍላል? ኤክሳይዝ ታክስ በተወሰኑ የምርት እና የአገልግሎት ባህሪ ባላቸ | ሰሌዳ | Seleda

ኤክሳይዝ ታክስ ማን ይከፍላል?

ኤክሳይዝ ታክስ በተወሰኑ የምርት እና የአገልግሎት ባህሪ ባላቸው ቁሳቁሶች እና አገልግሎቶች ላይ በዋናነት በአምራቾች እና አስመጪዎች ላይ የሚጣል ቀጥተኛ ያልሆነ የታክስ አይነት ቢሆንም እንደአለመታደል ሆኖ ከዋጋ ጋር ለሸማች አውርደው ይሰጡታል!

ጥያቄው ነባር ኤክሳይዝ ታክስ ሲቀነስ ከነባር ዋጋ መውረድ ያለመደው ገበያ (ገደብ የሌለው የትርፍ ጣሪያ ጭማሪ ፍላጎት) ባለበት የሸማች ጫና ይቀንሳል ወይ የሚለው ነው!

ታክስ ሊጨመርም ሊቀነስም ይችላል! ለምሳሌ ሀገራት ታክስ ለመጨመር ሲወስኑ የሚከተለው አመክንዮ ሊኖራቸው ይችላል ሊቀንሱ ሲያስቡም በተቃራኒው.....

መንግስታት በሁለት መንገድ ታክስን ሊጨምሩ ይችላሉ፤ አንደኛው የገቢ መጠናቸውን በመጨመር ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ለማዋል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የገንዘብ አቅርቦትን እና ፍላጎትን ለመቆጣጠር በሚያስቡበት ወቅት ነው፤ #ለምሳሌ የገንዘብ አቅርቦት በሰዎች እጅ ሲበዛ በታክስ ሰበብ መሰብሰብ የተለመደ አሰራር ነው፤ የገንዘብ አቅርቦትን ለመጨመር ታክስ መቀነስ ሌላው አሰራር ነው (ታክስ ተቀነሰ ማለት ሰዎች ለመንግስት ይከፍሉት የነበረው ገንዘብ እጃቸው ላይ ይቆያል ማለት ነው)።

በተጨማሪም ከውጪ በሚገቡ ቁሳቁሶች ላይ የሚጣል ታክስ የውጪ ምንዛሬን አቅርቦት መሰረት ያደረገ መሆን ስለሚኖርበት ሀገራት ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ  እጥረት ሲገጥማቸው ከውጪ በሚገቡ እና መሰረታዊ በማይባሉ ቁሶች ላይ ተጨማሪ ታክስ ይጥላሉ::

Via - The Ethiopian Economist View