Get Mystery Box with random crypto!

'የመኪና አስመጪዎች አዲስ ተሽከርካሪዎች ገበያ ላይ የሚሸጡበት ዋጋና ለገዥ የሚቆርጡት ደረሰኝ ሰፊ | ሰሌዳ | Seleda

"የመኪና አስመጪዎች አዲስ ተሽከርካሪዎች ገበያ ላይ የሚሸጡበት ዋጋና ለገዥ የሚቆርጡት ደረሰኝ ሰፊ ልዩነት እንዳለው በጥናቴ አረጋግጫለሁ " - የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በተሽከርካሪዎች ግብይትና አሰራር ዙሪያ ትላንት በሰጠው መግለጫ የተሽከርካሪዎች ግብይት መሬት ላይ ያለው እውነታ መንግስት ማግኘት የሚገባውን ገቢ መሠረት ያላደረገ መሆኑን በጥናቴ ደርሼበታለሁ ብሏል።

በዚህም መነሻ ከአስመጪዎችና ከዘርፉ ተሳታፊዎች ጋር ውይይት መደረጉንና ማንም በገበያ ዋጋ ደረሰኝ እንዲቆርጥና ገዢውም ትክክለኛ ደረሰኝ በመያዝ አገልግሎት ማግኘት እንዳለበት የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አሳስቧል።

ግብር ለመቀነስ በሚል አዲስ ተሽከርካሪዎች ገበያ ላይ ከሚሸጡበት ዋጋ በተቃራኒ የሃሰት ዋጋ ዝቅ አርጎ ደረሰኝ መቁረጥ በህግ ስለሚያስጠይቅ ሻጮች ከዚህ ድርጊት እንዲቆጠቡ ቢሮው በአፅንኦት አሳስበዋል።