Get Mystery Box with random crypto!

ሰሌዳ | Seleda

የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የሰርጥ አድራሻ: @seledadotio
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.47K
የሰርጥ መግለጫ

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@seleda_support ለማንኛውም አይነት ጥያቄ

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-06-09 07:47:11
በቀጣዩ በጀት አመት አዳዲስ የመንግስት ሰራተኛ ቅጥር አይፈፀምም ተባለ 

መንግስት ከአንድ ወር በኋላ ሃምሌ 2015ዓ.ም በሚጀምረው አዲሱ የ2016 ዓ.ም በጀት አመት ምንም አይነት የመንግስት ሰራተኛ ቅጥር እንደማይፈጸም የገንዘብ ሚንስቴር አስታውቋል፡፡

የገንዘብ ሚንስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ረቂቁን በተመለከተ ለፓርላማው ባቀረቡት ማብራሪያ  የ2016 የመደበኛ በጀት በየመ/ቤቱ ያለውን አዲሱን አደረጃጀት ታሳቢ በማድረግ፣ የበጀት አጠቃቀም በቁጠባና በውጤታማነት ላይ ያተኮረ እንደሚሆን ጠቅሰው በቀጣይ በጀት አመት አዳዲስ የመንግስት ሠራተኛ ቅጥር እንደማይኖር ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ በጀት መሆኑን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡

መንግስት አዘጋጅቶ ባቀረበው የ2016 በጀት ዓመት ካቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት ውስጥ ለመደበኛ ወጪዎች  370.1 ቢሊዮን ብር ፣ ለካፒታል ወጪዎች 203.4 ቢሊዮን ብር፣ለክልሎች የሚሰጥ የበጀት ድጋፍ  214  ቢሊዮን ብር፣ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ  14 ቢሊዮን ብር ሆኖ ቀርቧል፡፡
6.8K views04:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 20:43:44
በጉጂ ዞን እንጨት ተሸክሞ ሲሸጥ የነበረው የ7 አመት ልጅ ምስሉ በፌስቡክ ከተሰራጨ በኋላ አሜሪካ የመማር እድል አገኘ

ነገሩ እንዲህ ነው ገለታ ደምቦባ ይባላል 7 አመቱ ነው ጉጂ ዞን አዶላ ሬዴ የተባለ ወረዳ ጬምቤ የተባለ አከባቢ እንጨት ሲሸጥ ፎቶ ወጣ፣ ታሪኩን የተመለከተው አሜሪካ የአሪዞና ነዋሪው አበራ ቦጋለ የትንሹን ልጅ ታሪክ ለመቀየር መወሰኑን ለቢቢሲ ተናግሯል።

መጀመሪያ ላይ ልጁ እንጨት መሸጡን አቁሞ ወደ ትምህርት ቤት በመመለስ ከአንደኛ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ያለው ወጪ ለመሸፈን ነበር የወሰንኩት ይላሉ አቶ አበራ  ከቤተሰቦቻቸው ጋር ከተወያዩ በኋላ ህፃኑን እዚያ ማስተማር የብላቴናው ቤተሰብ ችግር ውስጥ ስላለ ውጤታማ ሊሆን እንደማይችል ተስማማን ብለዋል።

«ከቤተሰቦቼና ከቤተሰቡ ጋር ተነጋግረን ልጁን ወደ አሜሪካ ወስደን ለማሳደግ ተስማማን» ብለዋል። ልጁ እንጨት በመልቀም አንድ ሰዓት በእግር ተጉዞ ከተማ እንጨት ይሸጥ ነበር። የሕፃኑ አባት አቶ ዳምቦቢ ዎዲቦ ለቢቢሲ እንደተናገሩት አቶ አበራ ለልጁ ያሳየው መልካምነት እሱን ብቻ ሳይሆን የመንደሩን ነዋሪዎችንም አስደስቷል ብሏል።
7.3K views17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 18:38:40
ኢትዮጵያዊቷ አሰልጣኝ የላይቤርያን ብሄራዊ ቡድን ልትረከብ ነው

ኢትዮጵያዊቷ ኢንስትራክተር ሰላም ዘራይ የላይቤሪያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድንን በአሰልጣኝነት ለመረከብ ከስምምነት መድረሷ ለማወቅ ተችሏል።

አሰልጣኝ ሰላም ዘራይ አሁን ላይ ኮምቦልቻ ከተማ ስልጠና በመስጠት ላይ እንደምትገኝ እና በቅርቡ ወደ ስፍራው በማቅናት ለብሔራዊ ቡድኑ ፊርማዋን እንደምታኖር ታውቋል።
7.3K views15:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 18:01:33
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በ 10 ወራት ዉስጥ 3 ሚሊዮን ደምበኞች ማግኘቱን አስታወቀ

በመስከረም ወር መጨረሻ በአዲስአበባ አገልግሎት መስጠት የጀመረዉ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እስካሁን ሶስት ሚሊዮን ደምበኞች ማፍራቱን አስታውቋል።

በዛሬዉ እለትም ኩባንያዉ "ተረክ በጉርሻ" ሲል በሰየመዉ የደምበኞቹ እጣ ሽልማት መርሐግብር እድለኛ የሆኑ ተጠቃሚዎቹን ሸልሟል።

በ ሶስተኛ እና አራተኛ ዙር አሸናፊ የሆኑ ባለእድለኛ ደምበኞቹን አንድ ዘመናዊ የቤት መኪና ፣ አንድ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ ባጃጅ ፣ አንድ ባለ ሁለት እግር ተሽከርካሪ ሞተርሳይክል እና የተለያዩ የእጅ ሞባይል እና የታብሌት ሽልማቶችን ለባለእድለኛ ደምበኞቹ አበርክቷል።
7.3K views15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 16:52:42
አሜሪካ ከኢትዮጵያ ምድር በፈረንጆቹ 2030 ኤች አይ ቪን ለማጥፋት የሚውል የ112 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገች

አሜሪካ በኢትዮጵያ የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የሚውል ተጨማሪ የ112 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አድርጋለች፡፡

ድጋፉ በአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች የአስቸኳይ ጊዜ የኤች አይ ቪ ኤድስ ማገገሚያ እቅድ ፕሮግራም (ፔፕፋር) በኩል የሚተገበር ሲሆን፥ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2030 ኤች አይ ቪ ኤድስን ለማጥፋት የምታደርገውን ጥረት ለማገዝ የሚውል መሆኑ ታውቋል።
7.1K views13:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-22 13:07:48
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለስራ ፈጣሪዎች ያለማስያዣ ድጋፍ ሊያደርግ ነዉ ተባለ።

ባንኩ ሀሳባቸዉ ተወዳዳሪ ሆኖ ላሸነፈ እና ወደምርት ቢገቡ አዋጪ ይሆናሉ ብሎ ላሰባቸዉ ስራ ፈጣሪዎች፣ ያለማስያዣ ድጋፍ ለማድረግ ከስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር መስማማቱን ኤፍ ኤም ዘግቧል።

ሚኒስቴሩ የስራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት በርካታ ስራዎችን እየተሰራ መሆኑን ጠቁሞ የተቋሙን አሰራሮች፣ፖሊሲዎችና ስትራቲጂዎች በመቀየስ ላይ ይገኛል አስታዉቋል።
540 views10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-22 10:37:09
የገቢዎች ሚኒስቴር ግብር ከፋዮች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበ።

ሚኒስቴሩ ፤ ማንነታቸው በውል ያልታወቁ ግለሰቦች እና ቡድኖች የተለያዩ የማደናገሪያ እና የማጭበሪያ መንገዶችን እንዲሁም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ስም እና ሀሰተኛ ማንነት በመጠቀም ግብር ከፋዮችን እያጭበረበሩ ይገኛሉ ብሏል።

ይህ የማጭበርበር ተግባር እየተሰራ ያለው የግብር ከፋዩን የስልክ አድራሻ በመጠቀም እንደሆነም ገቢዎች ሚኒስቴር ገልጿል።

የማጭበርበር ተግባሩ የሚፈፀመው እንዴት ነው ?

የግብር ከፋዮችን አድራሻ በመጠቀም ፦

1.  ለታማኝ ግብር ከፋይ የሚሰጠውን ሽልማት እንድትሸለሙ እናስመርጣችኋለን፣

2. የኦዲት ውሳኔ እናስቀንስላችኋለን፣

3.  ድርጅታችሁ ወንጀል መስራቱ ስለተደረሰበት በህግ እንዳትጠየቁ እናደርጋለን የሚሉና የመሳሰሉ የማስፈራራት እና የማግባባት ሙከራዎች እና ዘዴዎችን በመጠቀም ነው።

ገቢዎች ሚኒስቴር ይህ ድርጊት እየተፈፀመ መሆኑ በክትትል ለማወቅ እንደቻለ ገልጾ ግብር ከፋዮች የነዚህ መሰል የማጭበርበር ሙከራዎች ሰለባ እንዳይሆኑ አስጠንቅቋል።

ማንኛውም ግብር ከፋይ ይህ መሰል ሁኔታዎች ሲያጋጥሙትም በአቅራቢያው ለሚገኝ የግብር ሰብሳቢ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በአፋጣኝ ጥቆማ እንዲሰጥ አሳስቧል
2.5K views07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-22 09:12:00
ለደንበኛህ የሰጠኀው የወሊድ መቆጣጠሪያ ህክምና አልሰራም የተባለው ዶክተር በስህተት የተወለደው ህፃን 18 ዓመት እስኪሞላው ድረስ እንዲያሳድግ ተፈረደበት

በኮሎምቢያ የወሊድ መቆጣጠሪያ ህክምናን ብወስድም ልጅ ወልጃለሁ ያለው ግለሰብ በዶክተሩ ላይ ክስ መስርቷል፤ ፍርድ ቤቱም ህፃኑ 18 ዓመት እስኪሞላው ድረስ ዶክተሩ እንዲያሳድግ ውስኗል

የፍርድ ቤቱ ውሳኔ እንደሚያሳየው፣ ዶ/ር ናራንጆ ለታካሚው ቤተሰብ 92 ሚሊዮን ፔሶ (20,300 ዶላር) የሞራል ጉዳት፣ 60 ሚሊዮን ፔሶ (13,200 ዶላር) ህጋዊ ክፍያ እና 143 ሚሊዮን ፔሶ (31,500 ዶላር የልጅ ማሳደጊያ እንዲከፍል ወስኗል።

በዜናው የተገረሙ አንዳንዶቹ ዶክተሩ DNA ይመርመርልኝ ከሌላ ወንድ ይሆናል ያረገዘችው አይልም ወይ ብለዋል።
3.5K views06:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-22 08:30:08
ከቱሪዝም ዘርፍ ከ3 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

ባለፉት 9  ወራት ከቱሪዝም ዘርፍ 3 ነጥብ 06 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ሚኒስትሩ የውጭ ምንዛሪ ግኝትና የስራ ዕድሎችን በማስፋፋት የዘርፉን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ለማሳደግ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻ የሆኑትን የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች (ጎርጎራ፣ ወንጪ፣ ሀላላ ኬላ፣ ኮይሻ)፣ የጅማ አባጂፋር ቤተ-መንግስትና የስንቀሌ የቆርኬዎች መጠለያን በተሟላ መልኩ ወደ ስራ ለማስገባት በቅንጅት እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡
3.6K views05:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-22 07:58:09
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ኮፐንሀገን ዴንማርክ አዲስ በረራ በይፋ አስጀምሯል።

አየር መንገዱ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎቹን እያሰፋ ሲሆን አሁን የተጀመረው አዲስ በረራም ኢትዮጵያን ከዴንማርክ ብሎም ከአፍሪካ ለማስተሳሰር የላቀ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።

በረራው በሳምንት አምስት ጊዜ የሚኖር ሲሆን ፥ ኮፐንሀገን ለአየር መንገዱ በአውሮፓ 21ኛው፤ በአለም ዓቀፍ ደረጃ ደግሞ 134ተኛው መዳረሻው መሆኑን የዘገበው ኢዜአ ነው።
3.8K views04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ