Get Mystery Box with random crypto!

ሰሌዳ | Seleda

የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የሰርጥ አድራሻ: @seledadotio
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.47K
የሰርጥ መግለጫ

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@seleda_support ለማንኛውም አይነት ጥያቄ

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-06-12 13:15:33
ህጻን ገለታ ትላንትናና ዛሬ

ማህበራዊ ሚድያን ለበጎ ምግባር ከተጠቀምንበት ከግለሰብም በላይ ማህበረሰብን ይቀይራል። የህጻን ገለታ ታሪክም ለዚህ ምስክር ነው።
3.7K views10:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 12:50:57
ተፈቷል!

የፊልም ዳይሬክተሩ እና የጉማ የፊልም ሽልማት መሥራች CEO ዮናስ ብርሃነ መዋ ተፈቷል።
3.9K views09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 12:47:24
በመዲናዋ የድምጽ ብክለት ባስከተሉ 208 ተቋማት ላይ የተለያየ ርምጃ ተወሰደ

በከተማዋ የድምጽ ብክለትን ችግር ለመቀነስ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የድምጽ መለኪያ ማሽኖች ተገዝተው ጥቅም ላይ መዋላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል።

ባለስልጣኑ ለኢፕድ በሰጠው መረጃ መሰረት በመዲናዋ አዋኪ ድምጾችን የመለየት ቁጥጥር ከተጀመረ በኋላ 423 ቤቶች ላይ ድምጽ ተለክቶ ከዚህም ውስጥ 208ቱ ሕጉን ተላልፈው በመገኘታቸው የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። ከነዚህም ውስጥ ስድስት የንግድ ቤቶች ደግሞ ሙሉ በሙሉ እንዲታሸጉ ተደርጓል።
3.7K views09:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 12:01:43
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቻይና በሁለቱም ጾታ ድል አድርገዋል

በቻይና የላንዡ ከተማ በተካሄደ የወንዶች ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንደኛ እስከ ሰባተኛ ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል።

በሴቶች ደግሞ አትሌት ለተብርሃን ሃይላይ በአንደኝነት ስታጠናቅቅ አትሌት ታደለች በቀለ ሁለተኛ ሆና ጨርሳለች።
ኝነት አጠናቃለች።
4.0K views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 11:59:10
ማስተካከያ

ዛሬ ማለዳ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ "20ሺህ ሰራተኞችን ሊቀጥር ነዉ"በሚል የሚል መረጃ አድርሰ ነበር። ምንም እንኳን መረጃውን ጠዋት ዋዜማ ራዲዮ ከሰራው ዘገባ የወሰድን ቢሆንም የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ሀላፊ ወ/ሮ ተወዳጅ እሸቱ መረጃው የሀሰት እንደሆነ ለብስራት ራዲዮ ከሰጡት ቃለመጠይቅ መረዳት ችለናል።

በኩባንያዉ ስም ከተከፈቱ ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት የተሰራጨ መሆኑን ጨምረዉ ተናግረዋል። ሰሌዳም ለተፈጠረው የተሳሳተ የመረጃ ስርጭት ይቅርታ ትጠይቃለች
4.0K views08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 10:51:16
በቀጣይ ዓመት ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ወደ ኤሌክትሮኒክስ የግዢ ስርዓት እንደሚገቡ ተነገረ

በፀጥታ ችግር ሳቢያ ከመደበኛ አገልግሎታቸው ተስተጓጉለው ከነበሩ ዩኒቨርስቲዎች ውጪ ያሉት ዩኒቨርስቲዎች ወደ ኤሌክትሮኒክስ የግዢ ስርዓት እንዲገቡ እንደሚደረግ የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን አስታውቋል።

እስካሁን 44 ከሚሆኑ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የኤሌክትሮኒክስ የግዢ ስርዓትን ተግባራዊ ያደረጉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ብቻ መሆናቸውንም ባለስልጣኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልፀዋል፡፡
4.4K views07:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 08:30:51
የተሻሻለው የንግድ ሕግ ማስፈጸሚያ መመርያ በቅርቡ ሊወጣ ነው ተባለ

ከ60 ዓመታት በኋላ ተሻሽሎ የወጣውን አዲሱን የንግድ ሕግ ማስፈጸሚያ መመርያዎች ውስጥ የመጀመርያው በዚህ ዓመት ፀድቆ ሥራ ላይ እንደሚውል መነገሩን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

የንግድ ሕጉ ማስፈጸሚያ ይሆናል ተብሎ የመጀመርያው መመርያ፣ የአክሲዮን ማኅበራትን የሚመለከት ነው፡፡ በዚሁ መሠረት ‹‹የአክሲዮን ማኅበራት ክትትል፣ ድጋፍና ቁጥጥር መመሪያ›› በሚል የተዘጋጀው ረቂቅ መመርያ ተዘጋጅቶ በመጠናቀቁ በዚህ በጀት ዓመት ይፀድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በዚህ ረቂቅ መመርያ ዙሪያ ሪፖርተር ያነጋገርናቸው የረቂቅ መመርያው የሕግ ባለሙያዎች ይህ መመርያ እየወጣ ያለው የንግድ ሕጉን ለማስፈጸም ነው ብለዋል፡፡

የንግድ ሕጉ ላይ አክሲዮን ኩባንያዎችን በተመለተ ግልጽ ያልሆኑ፣ ያልተብራሩና በተግባርም የንግድ ሕጉ ከወጣ በኋላ ውዥንብር የፈጠሩ ነገሮች ስላሉ፣ እነዚህን ሁሉ ለማጥራት የሚያስችል መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡
5.1K views05:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 19:07:27
#picture_of_the_day

በሊጉ ለመቆየት ከባድ አጣብቂኝ ውስጥ የገባውን ወልቂጤ ከተማን ወንድ ሴት፤ ህፃን አዛውንት ሳይቀር በእስታድም እየተገኙ የክለቡ ደጋፊዎች የተለመደ ድጋፋቸውን እየሰጡት ነው።

እንዳለመታደል ሆኖ ዛሬም ክትፎዎቹ ከመቻል ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 ቢሸነፉም የደጋፊዎቹ ስሜት ግን ቀልብን ስቧል።

እግር ኳስ
6.7K views16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 17:26:58
"ከመሬት አግኝቼ ለባለቤቱ የመለስኩት 430 ሺህ ዶላር ፍቅርም ጥላቻም አድርሶብኛል"

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኛ የሆኑት አቶ አማረ ታደሰ፣ በተለያየ ጊዜ በጥሬ ገንዘብ እና በቼክ በአጠቃላይ 436 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በሚሠሩበት ስፍራ ተረስቶ በማግኘት ለባለቤቱ መመለሳቸውን ይናገራሉ።

ይኹን እንጂ በዚሁ በጎ ሥራቸውን የወደዷቸው እና ድርጊቱን ያደነቁላቸው የመኖራቸውን ያህል ድርጊቱን እንደ ሞኝነት የቆጠሩም እንዳሉ አቶ አማረ ታደሰ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ወቅት ተናግረዋል።

“ጓደኞቼም ሆኑ ዘመድ እንዲሁም 95 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ‘አንተ የማትለወጥ ሰው ነህ፤ አያልፍልህም። ለምን ትመልሳለህ?’ ብለውኛል” በማለት ያጋጠማቸውን አስረድተዋል።
7.1K views14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 13:36:12
ቡልጋሪያ በመጫን አቅሙና በመጠኑ ከዓለም አንደኛ ግዙፍ የሆነ ተሸከርካሪ ሰራች፡፡

ልዩ መለያው ቤልዜዜድ-75710 የተሰኘው ይህ የዓለማችን ግዙፍ ተሽከርካሪ ብቻውን እቃ ከመጫኑ በፊት 360 ሺህ ኪሎ ግራም የሚመዝን ሲሆን አንዱ ጎማ ብቻውን 5 ሺህ 500 ኪሎ ግራም ይመዝናል ተብሏል፡፡

ተሽከርካሪው በተለይም በማዕድን ማውጣት ስራ ለተሰማሩ ኩባንያዎች ዋነኛ ተመራጭ ነው የተባለ ሲሆን በዚህ ዘርፍ በዓለም ተመራጭ ለሆኑት ካተርፒላር፣ ሌብሄር እና ቡሴረስ ኩባያዎች ጥሩ ዜና እንዳልሆነ ተገልጿል፡፡

20 ሜትር ርዝመት ያለው ይህ ተሽከርካሪ እያንዳንዳቸው 2 ሺህ 300 የፈረስ ጉልበት ያላቸው ሀይል ሰጪ ሲሊንደሮች ሲኖሩት በሰዓት 60 ኪሎ ሜትር መጓዝ ይችላልም ተብሏል፡፡

ኩባንያው አሁን ላይ ሶስት ቤልኤዜድ-75710 ሞዴል ተሸከርካሪዎችን ያመረተ ሲሆን ሶስቱም ተሽከርካሪዎች በሩሲያ መገዛታቸውን አል ዓይን ፅፏል።
7.3K views10:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ