Get Mystery Box with random crypto!

'ከመሬት አግኝቼ ለባለቤቱ የመለስኩት 430 ሺህ ዶላር ፍቅርም ጥላቻም አድርሶብኛል' የኢትዮጵያ | ሰሌዳ | Seleda

"ከመሬት አግኝቼ ለባለቤቱ የመለስኩት 430 ሺህ ዶላር ፍቅርም ጥላቻም አድርሶብኛል"

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኛ የሆኑት አቶ አማረ ታደሰ፣ በተለያየ ጊዜ በጥሬ ገንዘብ እና በቼክ በአጠቃላይ 436 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በሚሠሩበት ስፍራ ተረስቶ በማግኘት ለባለቤቱ መመለሳቸውን ይናገራሉ።

ይኹን እንጂ በዚሁ በጎ ሥራቸውን የወደዷቸው እና ድርጊቱን ያደነቁላቸው የመኖራቸውን ያህል ድርጊቱን እንደ ሞኝነት የቆጠሩም እንዳሉ አቶ አማረ ታደሰ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ወቅት ተናግረዋል።

“ጓደኞቼም ሆኑ ዘመድ እንዲሁም 95 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ‘አንተ የማትለወጥ ሰው ነህ፤ አያልፍልህም። ለምን ትመልሳለህ?’ ብለውኛል” በማለት ያጋጠማቸውን አስረድተዋል።