Get Mystery Box with random crypto!

ቡልጋሪያ በመጫን አቅሙና በመጠኑ ከዓለም አንደኛ ግዙፍ የሆነ ተሸከርካሪ ሰራች፡፡ ልዩ መለያው | ሰሌዳ | Seleda

ቡልጋሪያ በመጫን አቅሙና በመጠኑ ከዓለም አንደኛ ግዙፍ የሆነ ተሸከርካሪ ሰራች፡፡

ልዩ መለያው ቤልዜዜድ-75710 የተሰኘው ይህ የዓለማችን ግዙፍ ተሽከርካሪ ብቻውን እቃ ከመጫኑ በፊት 360 ሺህ ኪሎ ግራም የሚመዝን ሲሆን አንዱ ጎማ ብቻውን 5 ሺህ 500 ኪሎ ግራም ይመዝናል ተብሏል፡፡

ተሽከርካሪው በተለይም በማዕድን ማውጣት ስራ ለተሰማሩ ኩባንያዎች ዋነኛ ተመራጭ ነው የተባለ ሲሆን በዚህ ዘርፍ በዓለም ተመራጭ ለሆኑት ካተርፒላር፣ ሌብሄር እና ቡሴረስ ኩባያዎች ጥሩ ዜና እንዳልሆነ ተገልጿል፡፡

20 ሜትር ርዝመት ያለው ይህ ተሽከርካሪ እያንዳንዳቸው 2 ሺህ 300 የፈረስ ጉልበት ያላቸው ሀይል ሰጪ ሲሊንደሮች ሲኖሩት በሰዓት 60 ኪሎ ሜትር መጓዝ ይችላልም ተብሏል፡፡

ኩባንያው አሁን ላይ ሶስት ቤልኤዜድ-75710 ሞዴል ተሸከርካሪዎችን ያመረተ ሲሆን ሶስቱም ተሽከርካሪዎች በሩሲያ መገዛታቸውን አል ዓይን ፅፏል።