Get Mystery Box with random crypto!

አፍሪካውያንን ከጦጣ ጋር ያነጻጸሩት አውሮፓዊው አምባሳደር ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደረገ ሮማ | ሰሌዳ | Seleda

አፍሪካውያንን ከጦጣ ጋር ያነጻጸሩት አውሮፓዊው አምባሳደር ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደረገ

ሮማኒያ አምባሳደር ድራጎስ ቲጋው ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ ጠርታ ይፋዊ ይቅርታዋንም አቅርባለች።

አምባሳደሩ አፍሪካውያንን ከጦጣ ጋር አነጻጽረውበታል የተባለውን ንግግር ያደረጉት ናይሮቢ ኬንያ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ሕንጻ ውስጥ ሚያዚያ 18/2015 ዓ.ም. ነው።

እንደ ኤአፍፒ የዜና ወኪል ዘገባ ከሆነ አምባሳደር ቲጋዉ አንድ ጦጣ በመስኮት ከተመለከቱ በኋላ፤ “የአፍሪካ ቡድን ተወካዮች ሊቀላቀሉን” ሲሉ አፊዘዋል ብሏል።

አምባሳደሩ ለንግግራቸው በግለሰብ ደረጃ ይቅርታ ጠይቀዋል ቢባልም ከትናንት በስቲያ አርብ አፍሪካውያን ዲፕሎማቶች ይፋዊ ይቅርታ እንዲደረግ መጠለያቸውን የኬንያው ስታንዳርድ ጋዜጣ ዘግቧል።