Get Mystery Box with random crypto!

ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ታክስ እንዲከፍሉ መጠየቃቸውን ተቃውሙ | ሰሌዳ | Seleda

ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ታክስ እንዲከፍሉ መጠየቃቸውን ተቃውሙ

የገቢዎች ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ባንኮች ለካፒታል ማሳደጊያ ካዋሉት ትርፍ ላይ ታክስ እንዲከፍሉ አቅርቦት የነበረውን ጥያቄ፣ ለኢንሹራስ ኩባንያዎች ማቅረቡ ተቃውሞ ማስነሳቱ ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

ለካፒታል የዋለ ትርፍ ላይ ታክስ መከፈል እንደሌለበት እየታወቀ፣ የገቢዎች ሚኒስቴር ትርፋቸውን ለካፒታል ማሳደጊያ ያዋሉ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች፣ ለካፒታል ማሳደጊያ ባዋሉት ትርፍ ላይ ተጨማሪ ታክስ እንዲከፍሉ ጥያቄ ማቅረቡ አግባብ እንዳልሆነ በማመልከት፣ ለሚመለከተው የመንግሥት አካል አቤት እያሉ ነው፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር ሰሞኑን ለኢንሹራንስ ኩባንያዎች ሊከፍሉት ይገባል ያለውን የገንዘብ መጠን ባስቀመጠው የጊዜ ገደብ እንዲከፍሉ እያሳሰባቸው ሲሆን የኢንሹራንስ ኩባንያዎቹ ግን ለካፒታል ማሳደጊያ ባዋሉት ትርፍ ላይ ታክስ እንዲከፍሉ ከገቢዎች ሚኒስቴር የቀረበላቸውን ጥያቄ አግባብ አለመሆኑን እያሳወቁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡