Get Mystery Box with random crypto!

በቀጣይ ዓመት ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ወደ ኤሌክትሮኒክስ የግዢ ስርዓት እንደሚገቡ ተነገረ በፀጥ | ሰሌዳ | Seleda

በቀጣይ ዓመት ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ወደ ኤሌክትሮኒክስ የግዢ ስርዓት እንደሚገቡ ተነገረ

በፀጥታ ችግር ሳቢያ ከመደበኛ አገልግሎታቸው ተስተጓጉለው ከነበሩ ዩኒቨርስቲዎች ውጪ ያሉት ዩኒቨርስቲዎች ወደ ኤሌክትሮኒክስ የግዢ ስርዓት እንዲገቡ እንደሚደረግ የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን አስታውቋል።

እስካሁን 44 ከሚሆኑ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የኤሌክትሮኒክስ የግዢ ስርዓትን ተግባራዊ ያደረጉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ብቻ መሆናቸውንም ባለስልጣኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልፀዋል፡፡