Get Mystery Box with random crypto!

የተሻሻለው የንግድ ሕግ ማስፈጸሚያ መመርያ በቅርቡ ሊወጣ ነው ተባለ ከ60 ዓመታት በኋላ ተሻሽሎ | ሰሌዳ | Seleda

የተሻሻለው የንግድ ሕግ ማስፈጸሚያ መመርያ በቅርቡ ሊወጣ ነው ተባለ

ከ60 ዓመታት በኋላ ተሻሽሎ የወጣውን አዲሱን የንግድ ሕግ ማስፈጸሚያ መመርያዎች ውስጥ የመጀመርያው በዚህ ዓመት ፀድቆ ሥራ ላይ እንደሚውል መነገሩን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

የንግድ ሕጉ ማስፈጸሚያ ይሆናል ተብሎ የመጀመርያው መመርያ፣ የአክሲዮን ማኅበራትን የሚመለከት ነው፡፡ በዚሁ መሠረት ‹‹የአክሲዮን ማኅበራት ክትትል፣ ድጋፍና ቁጥጥር መመሪያ›› በሚል የተዘጋጀው ረቂቅ መመርያ ተዘጋጅቶ በመጠናቀቁ በዚህ በጀት ዓመት ይፀድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በዚህ ረቂቅ መመርያ ዙሪያ ሪፖርተር ያነጋገርናቸው የረቂቅ መመርያው የሕግ ባለሙያዎች ይህ መመርያ እየወጣ ያለው የንግድ ሕጉን ለማስፈጸም ነው ብለዋል፡፡

የንግድ ሕጉ ላይ አክሲዮን ኩባንያዎችን በተመለተ ግልጽ ያልሆኑ፣ ያልተብራሩና በተግባርም የንግድ ሕጉ ከወጣ በኋላ ውዥንብር የፈጠሩ ነገሮች ስላሉ፣ እነዚህን ሁሉ ለማጥራት የሚያስችል መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡