Get Mystery Box with random crypto!

በመዲናዋ የድምጽ ብክለት ባስከተሉ 208 ተቋማት ላይ የተለያየ ርምጃ ተወሰደ በከተማዋ የድምጽ | ሰሌዳ | Seleda

በመዲናዋ የድምጽ ብክለት ባስከተሉ 208 ተቋማት ላይ የተለያየ ርምጃ ተወሰደ

በከተማዋ የድምጽ ብክለትን ችግር ለመቀነስ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የድምጽ መለኪያ ማሽኖች ተገዝተው ጥቅም ላይ መዋላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል።

ባለስልጣኑ ለኢፕድ በሰጠው መረጃ መሰረት በመዲናዋ አዋኪ ድምጾችን የመለየት ቁጥጥር ከተጀመረ በኋላ 423 ቤቶች ላይ ድምጽ ተለክቶ ከዚህም ውስጥ 208ቱ ሕጉን ተላልፈው በመገኘታቸው የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። ከነዚህም ውስጥ ስድስት የንግድ ቤቶች ደግሞ ሙሉ በሙሉ እንዲታሸጉ ተደርጓል።