Get Mystery Box with random crypto!

ሰሌዳ | Seleda

የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የሰርጥ አድራሻ: @seledadotio
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.47K
የሰርጥ መግለጫ

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@seleda_support ለማንኛውም አይነት ጥያቄ

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-06-11 12:31:41
አፍሪካውያንን ከጦጣ ጋር ያነጻጸሩት አውሮፓዊው አምባሳደር ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደረገ

ሮማኒያ አምባሳደር ድራጎስ ቲጋው ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ ጠርታ ይፋዊ ይቅርታዋንም አቅርባለች።

አምባሳደሩ አፍሪካውያንን ከጦጣ ጋር አነጻጽረውበታል የተባለውን ንግግር ያደረጉት ናይሮቢ ኬንያ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ሕንጻ ውስጥ ሚያዚያ 18/2015 ዓ.ም. ነው።

እንደ ኤአፍፒ የዜና ወኪል ዘገባ ከሆነ አምባሳደር ቲጋዉ አንድ ጦጣ በመስኮት ከተመለከቱ በኋላ፤ “የአፍሪካ ቡድን ተወካዮች ሊቀላቀሉን” ሲሉ አፊዘዋል ብሏል።

አምባሳደሩ ለንግግራቸው በግለሰብ ደረጃ ይቅርታ ጠይቀዋል ቢባልም ከትናንት በስቲያ አርብ አፍሪካውያን ዲፕሎማቶች ይፋዊ ይቅርታ እንዲደረግ መጠለያቸውን የኬንያው ስታንዳርድ ጋዜጣ ዘግቧል።
7.2K views09:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 10:41:14
ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ታክስ እንዲከፍሉ መጠየቃቸውን ተቃውሙ

የገቢዎች ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ባንኮች ለካፒታል ማሳደጊያ ካዋሉት ትርፍ ላይ ታክስ እንዲከፍሉ አቅርቦት የነበረውን ጥያቄ፣ ለኢንሹራስ ኩባንያዎች ማቅረቡ ተቃውሞ ማስነሳቱ ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

ለካፒታል የዋለ ትርፍ ላይ ታክስ መከፈል እንደሌለበት እየታወቀ፣ የገቢዎች ሚኒስቴር ትርፋቸውን ለካፒታል ማሳደጊያ ያዋሉ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች፣ ለካፒታል ማሳደጊያ ባዋሉት ትርፍ ላይ ተጨማሪ ታክስ እንዲከፍሉ ጥያቄ ማቅረቡ አግባብ እንዳልሆነ በማመልከት፣ ለሚመለከተው የመንግሥት አካል አቤት እያሉ ነው፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር ሰሞኑን ለኢንሹራንስ ኩባንያዎች ሊከፍሉት ይገባል ያለውን የገንዘብ መጠን ባስቀመጠው የጊዜ ገደብ እንዲከፍሉ እያሳሰባቸው ሲሆን የኢንሹራንስ ኩባንያዎቹ ግን ለካፒታል ማሳደጊያ ባዋሉት ትርፍ ላይ ታክስ እንዲከፍሉ ከገቢዎች ሚኒስቴር የቀረበላቸውን ጥያቄ አግባብ አለመሆኑን እያሳወቁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
7.1K views07:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 08:56:42
ኢትዮጵያዊቷ መዲና ኢሳ በፈረንሳይ በተካሄደ  የ5000ሜ ውድድር አሸነፈች

መዲና ኢሳ ያሸነፈችዉ 14:46'60 በሆነ ሰዓት ሲሆን ይህም በአለም ወጣቶች የ5000ሜ ሻምፒዮና መዲና የገባችበት ሰዓት የቦታው ፈጣን ሰዓት ሆናል::
7.0K views05:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 08:43:53
በሞዛምቢክ የተገኘ አንድ የከበረ ድንጋይ ክብረ ወሰን በሆነ ዋጋ መሸጡ ተሰማ::

በዓለም ጥቂት አካባቢዎች ብቻ ከሚሊየን ዓመታት አንድ ጊዜ ይገኛል የተባለው የከበረ ድንጋይ በኒው ዮርክ ገበያ  የዓለም ክብረ ወሰን በሆነ 35 ሚሊዮን ዶላር መሸጡን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ሩቢ እየተባለ የሚጠራውና ባለፈው ዓመት በሞዛምቢክ የተገኘውና  ከሉል ጋር ይመሳሰላል የተባለው ይሄው የከበረ ድንጋይ 101 ካራት ጥራት እንዳለውም ተሰምቷል፡፡
6.8K views05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 00:01:38
ማንቺስተር ሲቲዎች በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ ሆነዋል!

ማንችስተር ሲቲ ከኢንተር ሚላን ጋር ያደረገውን የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የውድድሩ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል።
7.2K views21:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 23:32:11 ጎልልል ማን ሲቲ  ሮድሪ

ማንችስተር ሲቲ 1-0 ኢንተር ሚላን
7.2K views20:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 22:53:36
በቱርክ ኢስታንቡል አሁንም ጎል የለም

የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ

እረፍት

ማንችስተር ሲቲ 0-0 ኢንተር ሚላን
7.3K viewsedited  19:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 20:00:11
#ችሎት

ዮናስ ከእስር ቢፈታም "ለዳግም ጥያቄ ትፈልጋለህ?" ተብሎ ድጋሚ መታሰሩ ተነገረ

የጉማ አዋርድ መሥራችና አዘጋጅ ፤ ዳይሬክተር ዮናስ ብርሃነ መዋ ትናንት " በ9ኛው የጉማ አዋርድ ዝግጅት ተጠናቆ ሳለ ፤ ... ለጥያቄ እፈልገዋለን " በማለት ቦሌ ትራፊክ መምሪያ በተለምዶ ስሙ "አንበሳ ጋራዥ" አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ታሰሮ ነበር።

ዛሬ ፣ ከቀኑ 5:00 ሰዓት ላይ 24 (ኮከብ አዳራሽ)  በሚገኘው ፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር። ፍ/ቤቱ በ 5,000 (በአምስት ሺህ ብር) ዋስትና ለቆት ነበር።

ይሁን እንጂ ከቀኑ 9:00 ሰዓት ጀምሮ ከፖሊስ ጣቢያ እንደወጣ ፤ "ለዳግም ጥያቄ ትፈልጋለህ?" ተብሎ  ወደ ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዱን እንዲሁም ሰኞ ፍ/ቤት እንደሚቀረብ ከቤተሰቡ ያገኘሁት መረጃ ይጠቁማል፡፡
7.7K views17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 19:25:38
በሕገ-ወጥ የወርቅ ምርትና ግብይት ተግባር ላይ ተሰማርተው የተገኙ 29 የውጭ ዜጎች እና ሁለት ኢትዮጵያውያን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መሆኑን የጠቀሰው የብሔራዊ መረጃና የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የማዕድን ዘርፉ በሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ የነበረው ድርሻ እየቀነሰ መምጣቱን ተከትሎ እንዲሁም በዘርፉ የሚታዩ ሕገ-ወጥ ድርጊቶች ወደ ብሔራዊ የደኅንነት ሥጋት እንዳይሸጋገሩ ችግሮችን የሚለይና መፍትሄ የሚያስቀምጥ ሀገር አቀፍ ካውንስል ተቋቁሞ ተግባራዊ አንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑንም ገልጿል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ወደ ሀገር ውስጥ በሕጋዊ ሽፋን ቢገቡም በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸው፤ ባልተፈቀደላቸው የሥራ መስክ መሰማራታቸው እንዲሁም በሕገ-ወጥ መንገድ በወርቅ ምርት፣ ግብይትና ወደ ውጪ ሀገር የማስተላለፍ ተግባር ላይ  ሲሳተፉ እንደነበር ማረጋገጥ እንደተቻለ አብራርቷል፡፡
7.2K views16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 01:05:53
አትሌት ለሜቻ ግርማ "የኬንያውያን ባህላዊ ስፖርት" የሚባለውን የ3 ሺህ መሰናክል ውድድር የአለም ሪከርድ ሰብሯል!

ለሜቻ የአለም የስፖርት ተንታኞችን ባስደነቀ መልኩ 7:52.11 በመግባት በፓሪሱ ዳይመንድ ሊግ ሪከሪዱን የራሱ ረድርጓል።
216 views22:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ