Get Mystery Box with random crypto!

#ችሎት ዮናስ ከእስር ቢፈታም 'ለዳግም ጥያቄ ትፈልጋለህ?' ተብሎ ድጋሚ መታሰሩ ተነገረ የጉ | ሰሌዳ | Seleda

#ችሎት

ዮናስ ከእስር ቢፈታም "ለዳግም ጥያቄ ትፈልጋለህ?" ተብሎ ድጋሚ መታሰሩ ተነገረ

የጉማ አዋርድ መሥራችና አዘጋጅ ፤ ዳይሬክተር ዮናስ ብርሃነ መዋ ትናንት " በ9ኛው የጉማ አዋርድ ዝግጅት ተጠናቆ ሳለ ፤ ... ለጥያቄ እፈልገዋለን " በማለት ቦሌ ትራፊክ መምሪያ በተለምዶ ስሙ "አንበሳ ጋራዥ" አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ታሰሮ ነበር።

ዛሬ ፣ ከቀኑ 5:00 ሰዓት ላይ 24 (ኮከብ አዳራሽ)  በሚገኘው ፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር። ፍ/ቤቱ በ 5,000 (በአምስት ሺህ ብር) ዋስትና ለቆት ነበር።

ይሁን እንጂ ከቀኑ 9:00 ሰዓት ጀምሮ ከፖሊስ ጣቢያ እንደወጣ ፤ "ለዳግም ጥያቄ ትፈልጋለህ?" ተብሎ  ወደ ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዱን እንዲሁም ሰኞ ፍ/ቤት እንደሚቀረብ ከቤተሰቡ ያገኘሁት መረጃ ይጠቁማል፡፡