Get Mystery Box with random crypto!

በሕገ-ወጥ የወርቅ ምርትና ግብይት ተግባር ላይ ተሰማርተው የተገኙ 29 የውጭ ዜጎች እና ሁለት ኢት | ሰሌዳ | Seleda

በሕገ-ወጥ የወርቅ ምርትና ግብይት ተግባር ላይ ተሰማርተው የተገኙ 29 የውጭ ዜጎች እና ሁለት ኢትዮጵያውያን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መሆኑን የጠቀሰው የብሔራዊ መረጃና የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የማዕድን ዘርፉ በሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ የነበረው ድርሻ እየቀነሰ መምጣቱን ተከትሎ እንዲሁም በዘርፉ የሚታዩ ሕገ-ወጥ ድርጊቶች ወደ ብሔራዊ የደኅንነት ሥጋት እንዳይሸጋገሩ ችግሮችን የሚለይና መፍትሄ የሚያስቀምጥ ሀገር አቀፍ ካውንስል ተቋቁሞ ተግባራዊ አንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑንም ገልጿል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ወደ ሀገር ውስጥ በሕጋዊ ሽፋን ቢገቡም በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸው፤ ባልተፈቀደላቸው የሥራ መስክ መሰማራታቸው እንዲሁም በሕገ-ወጥ መንገድ በወርቅ ምርት፣ ግብይትና ወደ ውጪ ሀገር የማስተላለፍ ተግባር ላይ  ሲሳተፉ እንደነበር ማረጋገጥ እንደተቻለ አብራርቷል፡፡