Get Mystery Box with random crypto!

ሰሌዳ | Seleda

የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የሰርጥ አድራሻ: @seledadotio
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.47K
የሰርጥ መግለጫ

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@seleda_support ለማንኛውም አይነት ጥያቄ

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-05-21 20:15:56
ማን ሲቲ ቼልሲን አሸንፏል... የማንችስተር ሲቲ ደጋፊዎች ሜዳውን ወሮታል!!

ማንችስተር ሲቲ 1-0 ቼልሲ
#አልቫሬዝ 12'
5.8K views17:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 17:31:41
ሰበር

የማህበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ቴሌቪዥን ታገደ

ሚዲያው  አንቀጽፅ 70 በመተላለፉ እንደታገደ  የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ገልጿል። ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ ስርጭት በማድረጉ ነው ሲል የእግድ ደብዳቤው ገልፇል።
6.7K views14:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 16:26:37
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሚዛን ዓለም የ10 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድርን ከ30 ደቂቃ በታች በማጠናቀቅ ታሪክ ሰራች፡፡

አትሌቷ በለንደን ’’ኮንቲነንታል ቱር’’ ላይ በተደረገው የ10 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ላይ ነው ከ30 ደቂቃ በታች (29 ደቂቃ 58 ሰከንድ 70ማይክሮ ሰከንድ) በመግባት በታሪክ 12ኛዋ እንስት በመሆን ታሪክ የሰራችው፡፡

ይህም ታሪክ የማይረሳው የኢትዮጵያ ድል ነው ሲሉ የዓለም አትሌቲክስ እና ሌሎች መገናኛ ብዙሃን አሞካሽተውታል፡፡
6.5K views13:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 15:22:06
ለሶስተኛው የቴሌኮም አገልግሎት ሰጭ ተቋም ፈቃድ ለመስጠት ጨረታ ሊወጣ ነው ተባለ።

በኢትዮጵያ ለሶስተኛው የቴሌኮም አገልግሎት ሰጭ ተቋም ፈቃድ ለመስጠት በሰኔ 2015 ዓ.ም ጨረታ ሊወጣ መሆኑን የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን አስታውቋል።

ከዚህ ቀደም ለሁለት አዳዲስ የቴሌኮም ተቋማት ፈቃድ ለመስጠት ቀደም ሲል ጨረታ ወጥቶ ሳፋሪኮም ኩባንያ በ2013 ዓ.ም የመጀመሪያውን ፈቃድ መውሰዱን የጠቀሰው ባለስልጣኑ በጨረታው ላይ ተሳትፎ የነበረው ኤምቲኤን ግሩፕ በወቅቱ አቅርቦት የነበረው ገንዘብ ከሳፋሪኮም አንጻር ልዩነቱ በመስፋቱ የሁለተኛው ፈቃድ ሳይሰጥ መቅረቱንም አስታውሷል።
6.6K views12:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 14:24:44
የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝን በቴሌ ብር እንዲከፈል መታቀዱ ተገለጸ

በባንኮች በኩል ተከፋይ የሚሆነውን የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ወደ ቴሌ ብር የሞባይል ገንዘብ ሥርዓት ለማሸጋገር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የተቋማቸውን የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ለፓርላማ ባቀረቡበት ወቀት ተናግረዋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም የመንግሥት የኤክትሮኒክስ ክፍያ ድርሻ ለመወጣት እንዲያስችለው የሪፎርም ሥራዎችን እየሠራ እንደሆነና ለአብነትም የታክስ ክፍያ አሰባሰብ ሥርዓቱ በቴሌ ብር እንዲከፈል የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋቱን አቶ አህመድ እንደጠቆመው ሪፖርተር ፅፏል፡፡
6.6K views11:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 12:16:29
የአገሪቱን የኮንስትራክሽን ዘርፍ በብቸኝነት የተቆጣጠሩት የቻይና ኮንትራክተሮች ናቸው ተባለ።

የአገር ውስጥ ኮንስትራክሽን ዘርፍ በአብዛኛው በውጭ ኮንትራክተሮች እየተያዘ መኾኑን ሪፖርተር የኢትዮጵያ ሥራ ተቋራጮች ማኅበርን ጠቅሶ ዘግቧል። የውጭ ኮንትራክተሮች የአገር ውስጥ ተቋራጮች ሊሠሯቸው የሚችሏቸውን ፕሮጀክቶች ሳይቀር በመቆጣጠራቸው፣ የአገር ውስጥ ተቋራጮች ከሥራ ውጭ ኾነዋል በማለት ማኅበሩ ማማረሩን ዘገባው ጠቅሷል።

በቅርቡ በተደረገ አንድ ጥናት፣ የአገር ውስጥ ሥራ ተቋራጮች በመንግሥታዊ ፕሮጀክቶች ያላቸው ድርሻ ሦስት በመቶ ብቻ እንደኾነ መታወቁን ማኅበሩ መግለጡን ዘገባው አመልክቷል። የአገሪቱን የኮንስትራክሽን ዘርፍ በብቸኝነት የተቆጣጠሩት የቻይና ኮንትራክተሮች እንደኾኑ ተገልጧል።
6.4K views09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 11:07:54
የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከ1.5 ትሪሊዮን ብር በላይ ጉዳትና ኪሳራ ማድረሱን መንግሥት ይፋ አደረገ

በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች በተለይም ማዕከሉን በትግራይ ክልል አድርጎ ለሁለት ዓመታት በተካሄደውና በሌሎች የተወሰኑ አካባቢዎች በነበረው ጦርነት፣ ከ1.5 ትሪሊዮን ብር በላይ የሚገመት ጉዳትና ኪሳራ በአገር ላይ መድረሱን ገንዘብ ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል።

ግንቦት 9 ቀን 2015 ዓ.ም. የገንዘብ ሚኒስቴርን የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረቡት ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ፣ ተቋማቸው በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች በተካሄደው ጦርነት የደረሰውን ጉዳትና የመልሶ ግንባታ ፍላጎት የተመለከተ የዳሰሳ ጥናት (Damage and Needs Assessment) በማከናወን፣ የጥናት ውጤቱን ለመንግሥት እንዳቀረበ ተናግረዋል።

በጥናት ግኝቱ መሠረትም ያጋጠመው አጠቃላይ ጉዳትና የኢኮኖሚ ኪሳራ በአጠቃላይ 28 ቢሊዮን ዶላር እንደሚሆን ሪፖርታቸው አመላክቷል። ይህም በወቅቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን ከ1.5 ትሪሊዮን ብር በላይ ነው።

ለቋሚ ኮሚቴው ያቀረቡት ሪፖርት ላይ ከተቀመጠው መረጃ መረዳት እንደተቻለው፣ ‹‹22 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) 20.4 በመቶ የሚገመት ጉዳት›› ደርሷል። 

via - Reporter
6.3K views08:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 09:26:53
Congratulations

ፀሐይ ገመቹ በህንድ ቤንጋሉሩ በተካሄደው የ10 ኪ ሜ የጎዳና ላይ  ውድድር  አሸነፈች

በህንድ ቤንጋሉሩ በተካሄደው የ10 ኪ ሜ የጎዳና ላይ  ውድድር ፀሐይ ገመቹ 31:38 በመግባት በአንደኝነት አጠናቃለች። ፎተን ተስፋዬ እና ደራ ዲዳ ሁለተኛና ሦስተኛ በመውጣት አጠናቀዋል።
6.2K views06:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 08:23:13
‹‹ባለስልጣኑም ሆነ ከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቤቶችን ያወያያል እንጂ የሚያዋጣህ ይህ ነው ብሎ ዋጋ አይወስንም››  - የአዲስ አበባ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን

የአዲስ አበባ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ፍቅርተ አበራ ሰሞኑን በህብረተሰቡ ዘንድ በስፋት እየተነሳ ስለላው የግል ትምህርት ቤቶች የክፍያ ጭማሪን በተመለከተ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።  

አዲስ ዘመን፡- የግል ትምህርት ቤቶች የክፍያ ጭማሪ ላይ ባለስልጣኑ ኃላፊነቱ እስከምን ድረስ ነው?

... ወይዘሮ ፍቅርተ ባለስልጣኑም ሆነ ከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቤትን ያወያያል እንጂ የሚያዋጣህ ይህ ነው ብሎ ዋጋ አይወስንም። ነገር ግን አገልግሎት የሚሰጠው ትምህርት ቤቱ ነው። አገልግሎት የሚቀበሉት ወላጆች ናቸው።

ማድረግ የሚቻለው ወላጆች እና ትምህርት ቤቱ ቁጭ ብለው እንዲወያዩ ማመቻቸት ነው። ይህ የሚደረገው ለሁሉም ሲባል ነው። ትምህርት ቤቱም ያለ አግባብ ክፍያ ጠይቆ ከሔዱበት ተቋም አይሆንም።

ወላጅ ልጆቹን ይዞ ከወጣ ባዶ ይሆናል፤ አይጠቀምም። ወላጅም በተመሳሳይ ልጁን ሌላ ትምህርት ቤት ካመጣ ፈተና ስለሚሆን ተወያዩ ተግባብታችሁ ቀጥሉ እያልን ነው። በዛ ላይ አብዛኛው ተስማምቷል።

ባልተስማሙት ላይ ደግሞ እኛ  ዋጋ ትመና ውስጥ ግን አንገባም። ከምንከተለው ስርዓት ጋርም የሚሔድ አይደለም።..."
6.5K views05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 21:37:09
ማንቸስተር ሲቲ የሻምፒዮን ሆነ

በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመሩት ማንችስተር ሲቲዎች የ 2022/23 የውድድር ዓመት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ማንችስተር ሲቲዎች ከቀሪ ሶስት ጨዋታዎች ሻምፒዮን ለመሆን ሁለቱን ማሸነፍ ቢጠበቅበትም ተከታያቸው አርሰናል ተከታታይ ሁለት ጨዋታዎችን መሸነፉን ተከትሎ ቀሪ ጨዋታዎች እየቀሯቸው ሻምፒዮን ለመሆን ችለዋል።
7.0K views18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ