Get Mystery Box with random crypto!

የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝን በቴሌ ብር እንዲከፈል መታቀዱ ተገለጸ በባንኮች በኩል ተከፋይ የሚ | ሰሌዳ | Seleda

የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝን በቴሌ ብር እንዲከፈል መታቀዱ ተገለጸ

በባንኮች በኩል ተከፋይ የሚሆነውን የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ወደ ቴሌ ብር የሞባይል ገንዘብ ሥርዓት ለማሸጋገር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የተቋማቸውን የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ለፓርላማ ባቀረቡበት ወቀት ተናግረዋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም የመንግሥት የኤክትሮኒክስ ክፍያ ድርሻ ለመወጣት እንዲያስችለው የሪፎርም ሥራዎችን እየሠራ እንደሆነና ለአብነትም የታክስ ክፍያ አሰባሰብ ሥርዓቱ በቴሌ ብር እንዲከፈል የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋቱን አቶ አህመድ እንደጠቆመው ሪፖርተር ፅፏል፡፡