Get Mystery Box with random crypto!

የአገሪቱን የኮንስትራክሽን ዘርፍ በብቸኝነት የተቆጣጠሩት የቻይና ኮንትራክተሮች ናቸው ተባለ። የ | ሰሌዳ | Seleda

የአገሪቱን የኮንስትራክሽን ዘርፍ በብቸኝነት የተቆጣጠሩት የቻይና ኮንትራክተሮች ናቸው ተባለ።

የአገር ውስጥ ኮንስትራክሽን ዘርፍ በአብዛኛው በውጭ ኮንትራክተሮች እየተያዘ መኾኑን ሪፖርተር የኢትዮጵያ ሥራ ተቋራጮች ማኅበርን ጠቅሶ ዘግቧል። የውጭ ኮንትራክተሮች የአገር ውስጥ ተቋራጮች ሊሠሯቸው የሚችሏቸውን ፕሮጀክቶች ሳይቀር በመቆጣጠራቸው፣ የአገር ውስጥ ተቋራጮች ከሥራ ውጭ ኾነዋል በማለት ማኅበሩ ማማረሩን ዘገባው ጠቅሷል።

በቅርቡ በተደረገ አንድ ጥናት፣ የአገር ውስጥ ሥራ ተቋራጮች በመንግሥታዊ ፕሮጀክቶች ያላቸው ድርሻ ሦስት በመቶ ብቻ እንደኾነ መታወቁን ማኅበሩ መግለጡን ዘገባው አመልክቷል። የአገሪቱን የኮንስትራክሽን ዘርፍ በብቸኝነት የተቆጣጠሩት የቻይና ኮንትራክተሮች እንደኾኑ ተገልጧል።