Get Mystery Box with random crypto!

‹‹ባለስልጣኑም ሆነ ከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቤቶችን ያወያያል እንጂ የሚያዋጣህ ይህ ነው ብሎ ዋ | ሰሌዳ | Seleda

‹‹ባለስልጣኑም ሆነ ከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቤቶችን ያወያያል እንጂ የሚያዋጣህ ይህ ነው ብሎ ዋጋ አይወስንም››  - የአዲስ አበባ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን

የአዲስ አበባ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ፍቅርተ አበራ ሰሞኑን በህብረተሰቡ ዘንድ በስፋት እየተነሳ ስለላው የግል ትምህርት ቤቶች የክፍያ ጭማሪን በተመለከተ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።  

አዲስ ዘመን፡- የግል ትምህርት ቤቶች የክፍያ ጭማሪ ላይ ባለስልጣኑ ኃላፊነቱ እስከምን ድረስ ነው?

... ወይዘሮ ፍቅርተ ባለስልጣኑም ሆነ ከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቤትን ያወያያል እንጂ የሚያዋጣህ ይህ ነው ብሎ ዋጋ አይወስንም። ነገር ግን አገልግሎት የሚሰጠው ትምህርት ቤቱ ነው። አገልግሎት የሚቀበሉት ወላጆች ናቸው።

ማድረግ የሚቻለው ወላጆች እና ትምህርት ቤቱ ቁጭ ብለው እንዲወያዩ ማመቻቸት ነው። ይህ የሚደረገው ለሁሉም ሲባል ነው። ትምህርት ቤቱም ያለ አግባብ ክፍያ ጠይቆ ከሔዱበት ተቋም አይሆንም።

ወላጅ ልጆቹን ይዞ ከወጣ ባዶ ይሆናል፤ አይጠቀምም። ወላጅም በተመሳሳይ ልጁን ሌላ ትምህርት ቤት ካመጣ ፈተና ስለሚሆን ተወያዩ ተግባብታችሁ ቀጥሉ እያልን ነው። በዛ ላይ አብዛኛው ተስማምቷል።

ባልተስማሙት ላይ ደግሞ እኛ  ዋጋ ትመና ውስጥ ግን አንገባም። ከምንከተለው ስርዓት ጋርም የሚሔድ አይደለም።..."