Get Mystery Box with random crypto!

ሰሌዳ | Seleda

የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የሰርጥ አድራሻ: @seledadotio
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.47K
የሰርጥ መግለጫ

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@seleda_support ለማንኛውም አይነት ጥያቄ

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 149

2022-11-03 14:51:34
ኢትዮ ቴሌኮም በጦርነቱ የቴሌኮም አገልግሎት ተቋርጦባቸው በነበሩ አካባቢዎች  አገልግሎቸት ሊያስጀምር ነው።

የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ እንዳስታወቁት፣ በቆቦ፣ ሮቢት፣ ዞብል፣ ጎቢዬና ዋጃ የመልሶ ጥገና ተከናውኖ የቴሌኮም አገልግሎት የጀመረ ሲሆን፣ እንዲሁም በዛሬው ዕለት አድርቃይ ላይ አገልግሎቱ መጀመሩን አስታውቀዋል።

በአላማጣና ኮረም አካባቢዎች እንዲሁ የቴሌኮም አገልግሎቱ በአጠረ ሰአት ይጀምራል ተብሏል። ኩባንያው የጥገና ባለሙያዎችን አሰማርቶ የተቋረጠውን አገልግሎት ካስጀመረ ሁለት ሳምንታት እንዳስቆጠረ ያስታወቀ ሲሆን፣ በቀሪ አካባቢዎች የሚደረገው ጥገና እግር በእግር የሚቀጥል መሆኑ ተገልጿል።
3.6K views11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-03 11:23:17
ድርጅቱ ከ2 ቢሊዮን በላይ ብር የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን  ከሀገር ውስጥ ሊያቀርብ ነው።

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (ኢግልድ) ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን ከሀገር ውስጥ፤ የ 18 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር ግብዓቶችን ከውጭ በማስገባት ለተጠቃሚዎች የሚያቀርብ መሆኑን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሮ የሺመቤት ነጋሽ በዘርፉ የሚታየውን እጥረት ለመቅረፍ የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን ከውጭ እና ከአገር ውስጥ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ገልጸዋል። ይህንን ዕቅድ ለማሳካት ያመች ዘንድ የሥራ ካፒታልን በማሳደግ የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን የማቅረብ አቅምን ለማሳደግ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋር ውይይት ተደርጓል ያሉት ወይዘሮ የሺመቤት፤ በቂ የሥራ ካፒታል ባለመኖሩ ባለፈው ዓመት የሚፈለገውን ያህል ግብዓት ማቅረብ ባለመቻሉ ይህን ሁኔታ ለማሻሻል መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

እንደ ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ፤ ድርጅቱ በከፍተኛ የዋጋ ንረት ምክንያት የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ በትኩረት እየሠራ ነው። ለአብነትም ባለፈው ዓመት ግምቱ 19 ሚሊዮን ዶላር የሚሆን ዘይት ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባ አድርጓል። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የኢትዮጵያን የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ አቅም ለማሳደግ በመላ ሀገሪቱ በ83 ቅርንጫፎች እየሠራ ይገኛል።
5.1K views08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-03 09:18:24
ሩሲያ አቋርጣው ወደነበረው የጥቁር ባህር ስንዴ ማጓጓዝ ስምምነት ተመለሰች።

ሩሲያ ዩክሬን የእህል ምርቷን ለውጭ ገበያ እንድታቀርብ ቀደም ሲል ወደተደረሰው ስምምነት እንደገና መመለሷን ዓለማቀፍ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ሩሲያ ይህንኑ ስምምነቷን የገለጸችው፣ ፕሬዝዳንት ፑቲን እና የቱርኩ አቻቸው ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ከተወያዩ በኋላ ነው።

ዩክሬን በጥቁር ባሕር ላይ በሚንቀሳቀሱ መርከቦች ላይ የድሮን ጥቃት ላለመፈጸም ዋስትና መስጠቷ፣ ሩሲያ ከአምስት ቀናት በፊት ራሷን ወዳገለለችበት ስምምነት እንድትመለስ ምክንያት እንደሆናት ገልጻለች ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
5.5K views06:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-03 08:01:27
በይርጋለም ኢንዱስትሪ ፓርክ ለሚያለሙ ባለሀብቶች መሬት በድርድር ሊቀርብ ነው

በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ ለማልማት ፍላጎት ላሳዩ ባለሀብቶች መሬት በድርድር እንዲሁም በዝቅተኛ ዋጋ ለማቅረብ መታቀዱን የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታውቋል፡፡ ፓርኩ ባለሀብቶቹ የሚሰማሩበትን ዘርፍ የፍላጎት ማሳወቂያ ቅጽ ከመሙላት ባሻገር የቢዝነስ ዕቅዳቸውን በማቅረብ ላይ መሆናቸውን አሳውቋል፡፡

የይርጋለም የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ያለውን የኢንቨስትመንት ዕድልና አማራጮችን ለአገር ውስጥና ለውጭ ባለሀብቶች ማስተዋወቅ ዓላማው ያደረገ የኢንቨስትመንት ማስተዋወቂያ መድረክ ባለፈው ሳምንት በሐዋሳ ከተማ መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን፣ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚና የበላይነህ ክንዴ ቢዝነስ ግሩፕ ባለቤትን ጨምሮ ከ106 በላይ ባለሀብቶች በፓርኩ ገብተው ለማልማት ፍላጎታቸውን ገልጸዋል ተብሏል፡፡

በመድረኩ የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ የተለያዩ የግብርና ምርቶችን ከአርሶ አደሩ በመቀበል የአቮካዶ ዘይት፣ ወተት፣ ማርና ቡናን በማቀነባበር ለአገር ውስጥና ውጭ ገበያ የሚያቀርቡ ፋብሪካዎችን ወደ ተግባር ማስገባቱ የተገለፀ ሲሆን ለአብነትም በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ፓርኩ ውስጥ የሚገኙት ፋብሪካዎች ወደ ውጭ ከላኩት ምርት 2.6 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ከመገኘቱም ባሻገር ከ140 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ አርሶ አደሮች የገበያ ትስስር መፍጠሩ ተጠቁሟል፡፡

via - reporter
5.9K views05:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 18:18:56
ኢትዮ ቴሌኮም የኢንተርኔት መቆራረጥ ችግር እንደሚኖር ገለፀ።

ኢትዮ ቴሌኮም ምሽቱን ለደንበኞቹ ባስተላለፈው መልዕክት “ከሀገር ውጪ (በጅቡቲ) በኩል በሚያልፉ የኢንተርኔት መገናኛ መስመር ላይ ባጋጠመ ችግር” ባለው ምክንያት የኢንተርኔት አገልግሎቱ ሊቆራረጥ ይችላል ብሏል።

በአሁን ሰዓት የኢንተርኔት አገልግሎቱ በመጠባበቂያ መስመሮች ብቻ እየሰራ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን አገልግሎቱን ለማስቀጠል ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል። ችግር የተፈጠርበት መስመር ከፍተኛ ባንድዊድዝ ተሸካሚ ዓለም አቀፍ ባህር ጠለቅ የኢንተርኔት መገናኛ መስመር መሆኑንም ኩባን ያው ገልጿል።
7.7K views15:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 15:31:46
የአገሪቱ የስንዴ ፍላጎት ተሸፍኖ አሥር ሚሊዮን ኩንታል ትርፍ ምርት እንደሚገኝ ተገለጸ።

ዘንድሮ በመኸርና በበጋ መስኖ የሚለማው የስንዴ ምርት ለአገር ውስጥ ፍጆታ ከመዋል አልፎ አሥር ሚሊዮን ኩንታል ትርፍ የሚገኝበት መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው፣ የ2014/15 የመኸር ምርት ዘመን ሰብል በዚህ ወቅት እየተሰበሰበ ሲሆን፣ ይገኛል ተብሎ ከሚጠበቀው 108 ሚሊዮን ኩንታል የስንዴ ምርት ባሻገር በበጋ መስኖ 52 ሚሊዮን  ኩንታል እንደሚገኝና በድምሩ 160 ሚሊዮን ኩንታል ምርት አገሪቱ ታገኛለች ተብሎ ይጠበቃል ተብሏል፡፡

የአገሪቱ የሕዝብ ቁጥር ግንዛቤ ውስጥ ገብቶ፣ በተጨማሪም በየዓመቱ የሚያድገውን የአገር ውስጥ የፍጆታ መጠን በትክክል በማስላት በ2015 ዓ.ም. 97 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ለአገር ውስጥ ፍጆታ እንደሚያስፈልግ መረዳቱን ያስታወቀው የግብርና ሚኒስቴር፣ ይህንን ዝርዝር ጥናት በርካታ ኢኮኖሚስቶችና የሰብል ልማት ሰዎች ያጠኑት ስለመሆኑ ገልጿል፡፡

‹‹ሌላው ቢቀር በመኸርና በመስኖ ብንሠራ 107 ሚሊዮን ኩንታል ማምረት እንችላለን፣ በጣም በዝቅተኛ ግምት ነው ይህንን የገመትነው፡፡ ይህን ብቻ በማሰብ አሥር ሚሊዮን ኩንታል ትርፍ ምርት አለን፤›› ያሉት በግብርና ሚኒስቴር የእርሻና ሆልቲካልቸር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ መለሰ መኮንን (ዶ/ር)፣ በድምሩ በመኸርና በመስኖ የሚለማው የምርት መጠን ከታቀደው በላይ እንደሚሆን አስረድተዋል፡፡ ‹‹አሥር ሚሊዮን አይደለም ከዚያ በላይ ትርፍ ማምረት የምንችልበት ዕድል አለ፡፡ ይህንንም ኤክስፖርት ማድረግ የምንችልበት ዕድል አለ፤›› ሲሉ  ሚኒስትር ዴኤታው መናገራቸውን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡
7.8K views12:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 13:35:35
ባንኮች ከሚያበድሩት 20 በመቶውን የግምጃ ቤት ሰነድ እንዲገዙበት የሚያስገድድ መመርያ ፀደቀ።

ሁሉም የንግድ ባንኮች ከሚለቁት ብድር ውስጥ 20 በመቶውን በየወሩ ወደ መንግሥት የግምጃ ቤት ሰነድ ግዥ ፈሰስ እንዲያደርጉ የሚያስገድድ መመርያ መፅደቁን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡ ከትናንት ጥቅምት 22 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የሆነው መመርያ፣ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ውጪ በሁሉም ባንክ ላይ ተግባራዊ ይሆናል፡፡

ባንኮቹ ያበደሩትን 20 ከመቶን በየወሩ እያሠሉ የግምጃ ቤት ሰነድ የሚገዙበት ገንዘብ ተጠራቅሞ አምስተኛው ዓመት ላይ የሚመለስላቸው ሲሆን፣ የወለድ መጠኑም ከተቀማጭ ወለድ ላይ ሁለት ከመቶ በመጨመር ይሆናል፡፡ ካለፈው ዓመት መስከረም ወር ጀምሮ ባንኮች የጠቅላላ ዓመታዊ ብድራቸውን አንድ በመቶ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክን ቦንድ እንዲገዙበት የሚያዘው መመርያ እየተተገበረ ሲሆን፣ ይህ መመርያ ለአሥር ዓመታት የሚቀጥል ነው፡፡

አዲስ ከወጣው መመርያ ጋር ባንኮች በአጠቃላይ ከሚያበድሩት 21 በመቶውን ወደ መንግሥት ፋይናንስ ፈሰስ ያደርጋሉ ማለት ነው፡፡ ከዚሁ በተጓዳኝ ባንኮች ሰባት ከመቶ መጠባበቂያ ገንዘብ ማስቀመጥ እንዳለባቸው ይታወቃል፡፡ ስለዚህ በአጠቃላይ ባንኮች ከሚሰበስቡት ጠቅላላ ተቀማጭ ውስጥ 28 በመቶውን በተለያየ ምክንያት መልሰው ለማበደር ሊጠቀሙት አይችሉም ማለት ነው፡፡

አዲሱ መመርያ ከዚህ ቀደም ባንኮች ይሰጡ ከነበረው የ27 በመቶ ግዴታ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን፣ ልዩነቱ ይኼኛው በየወሩ መሆኑ፣ ወለዱ ከፍ ማለቱና ከባንኮች የተሰበሰበው የግምጃ ቤት ሰነድ መግዣ ገንዘብ በንግድ ባንክ በኩል ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች መሰጠቱ ነው፡፡ አዲሱ መመርያ ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያት የመንግሥትን የበጀት ጉድለት ለመሸፈን መሆኑ ታውቋል፡፡

via - reporter
7.6K views10:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 12:05:33
ከኅዳሴ ግድብ የሚመረተው ኃይል ወደ ዋናው ግሪድ እንዲገባ የሚካሄደው የመስመር ጥገና እና ፍተሻ ሥራ በቀጣይ ሣምንት ይጀመራል ተባለ።

የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ በኦሮሚያ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የሚገኙ ከ30 በላይ ወረዳዎችን አቆራርጦ አዲስ አበባ እንደሚገባም ነው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ። በዚህ ርቀት ውስጥ በሚሰሩ ሥራዎች የክልሎቹ የጸጥታ ኃይሎች እና መላው ነዋሪ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግም ጠይቋል።

በሌላ በኩል የኢትዮ ኬንያ የኤሌክትሪክ የኃይል ሽያጭን ለማከናወን ዝግጅቱ የተጠናቀቀ ሲሆን፥ በቀጣይ ቀናቶች የኃይል ሽያጩ ይጀመራል ተብሏል። በመጀመሪያው ሽያጭም 200 ሜጋ ዋት ኃይል ይቀርባል ነው የተባለው። የኃይል ግዢ ስምምነቱ ባለፈው ነሐሴ ወር መፈረሙ የሚታወስ ነው።

via - fbc
7.1K views09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 10:41:03
ከፍተኛ የዋጋ ንረት የታየባቸው የአለም ሀገራት ደረጃ ይፋ ሆነ።

በመጠናቀቅ ላይ ባለው የፈረንጆቹ አመት 2022 ከፍተኛ የዋጋ ንረት የታየባቸውን የአለም ሀገራት ጆን ሆፕኪንስ ዩንቨርሲቲ ይፋ አድርጓል። በዚህም መሰረት ደቡብ አፍሪካዊቷ ሀገር ዚምባቡዌ 393 በመቶ አመታዊ የዋጋ ንረት በማስመዝገብ ከአለም ሀገራት ቀዳሚውን ስፍራ ይዛለች።

ሌላኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ጋና በሁለተኝነት ስትከተል ኩባ፤ ቱርክና ስሪላንካ እስከ አምስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል። እንደ ዩንቨርስቲው ጥናት ከሆነ በአለም ላይ ከፍተኛ የዋጋ ንረት ካስመዘገቡ ሃያ ሶስት ሀገራት አስራ አንዱ የአፍሪካ አገራት ናቸው።  ከስድስተኛ እስከ ሀያ ሶስተኛ ያሉትን በምስሉ ላይ ይመልከቱ።
7.3K views07:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 09:48:20
ህገወጦችን ህብረተሰቡ እንዲያጋልጥ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ (ኢብባ) ጥሪ ማቅረቡን ተከትሎ በከፍተኛ ሁኔታ ጥቆማ እየመጣ መሆኑ ታወቀ፡፡

ከሳምንታት በፊት ኢብባ ዜጎች በህገወጥ የምንዛሬ ገበያ፣ ህገወጥ ሃዋላ፣ ህገወጥ የወርቅ ንግድ፣ የህገወጥ የገንዘብ ህትመት የሚያከናውኑ አካላትን ለሚጠቁም ወሮታ እንዳዘጋጀ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ለዚህም ይረዳ ዘንድ የተለያዩ የመጠቆሚያ ዘዴዎችን ያስተዋወቀ ሲሆን ጥቆማ እየደረሰው መሆኑን ካፒታል ከባንኩ ምንጮች ያገኘችው መረጃ ያሳያል፡፡ ስለጉዳዩ የመግለጽ ሃላፊነት የሌላቸው አንድ ሃላፊ እንዳሉት ከኢብባ ጥሪ በኋላ ጥቆማ በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ማእከላዊ ባንኩ እየመጣ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

via - Ethiopian Business Daily
6.9K views06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ