Get Mystery Box with random crypto!

ድርጅቱ ከ2 ቢሊዮን በላይ ብር የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን  ከሀገር ውስጥ ሊያቀርብ ነው። የኢትዮጵ | ሰሌዳ | Seleda

ድርጅቱ ከ2 ቢሊዮን በላይ ብር የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን  ከሀገር ውስጥ ሊያቀርብ ነው።

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (ኢግልድ) ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን ከሀገር ውስጥ፤ የ 18 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር ግብዓቶችን ከውጭ በማስገባት ለተጠቃሚዎች የሚያቀርብ መሆኑን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሮ የሺመቤት ነጋሽ በዘርፉ የሚታየውን እጥረት ለመቅረፍ የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን ከውጭ እና ከአገር ውስጥ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ገልጸዋል። ይህንን ዕቅድ ለማሳካት ያመች ዘንድ የሥራ ካፒታልን በማሳደግ የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን የማቅረብ አቅምን ለማሳደግ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋር ውይይት ተደርጓል ያሉት ወይዘሮ የሺመቤት፤ በቂ የሥራ ካፒታል ባለመኖሩ ባለፈው ዓመት የሚፈለገውን ያህል ግብዓት ማቅረብ ባለመቻሉ ይህን ሁኔታ ለማሻሻል መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

እንደ ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ፤ ድርጅቱ በከፍተኛ የዋጋ ንረት ምክንያት የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ በትኩረት እየሠራ ነው። ለአብነትም ባለፈው ዓመት ግምቱ 19 ሚሊዮን ዶላር የሚሆን ዘይት ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባ አድርጓል። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የኢትዮጵያን የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ አቅም ለማሳደግ በመላ ሀገሪቱ በ83 ቅርንጫፎች እየሠራ ይገኛል።