Get Mystery Box with random crypto!

ሩሲያ አቋርጣው ወደነበረው የጥቁር ባህር ስንዴ ማጓጓዝ ስምምነት ተመለሰች። ሩሲያ ዩክሬን የእህ | ሰሌዳ | Seleda

ሩሲያ አቋርጣው ወደነበረው የጥቁር ባህር ስንዴ ማጓጓዝ ስምምነት ተመለሰች።

ሩሲያ ዩክሬን የእህል ምርቷን ለውጭ ገበያ እንድታቀርብ ቀደም ሲል ወደተደረሰው ስምምነት እንደገና መመለሷን ዓለማቀፍ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ሩሲያ ይህንኑ ስምምነቷን የገለጸችው፣ ፕሬዝዳንት ፑቲን እና የቱርኩ አቻቸው ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ከተወያዩ በኋላ ነው።

ዩክሬን በጥቁር ባሕር ላይ በሚንቀሳቀሱ መርከቦች ላይ የድሮን ጥቃት ላለመፈጸም ዋስትና መስጠቷ፣ ሩሲያ ከአምስት ቀናት በፊት ራሷን ወዳገለለችበት ስምምነት እንድትመለስ ምክንያት እንደሆናት ገልጻለች ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡