Get Mystery Box with random crypto!

በይርጋለም ኢንዱስትሪ ፓርክ ለሚያለሙ ባለሀብቶች መሬት በድርድር ሊቀርብ ነው በይርጋለም የተቀና | ሰሌዳ | Seleda

በይርጋለም ኢንዱስትሪ ፓርክ ለሚያለሙ ባለሀብቶች መሬት በድርድር ሊቀርብ ነው

በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ ለማልማት ፍላጎት ላሳዩ ባለሀብቶች መሬት በድርድር እንዲሁም በዝቅተኛ ዋጋ ለማቅረብ መታቀዱን የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታውቋል፡፡ ፓርኩ ባለሀብቶቹ የሚሰማሩበትን ዘርፍ የፍላጎት ማሳወቂያ ቅጽ ከመሙላት ባሻገር የቢዝነስ ዕቅዳቸውን በማቅረብ ላይ መሆናቸውን አሳውቋል፡፡

የይርጋለም የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ያለውን የኢንቨስትመንት ዕድልና አማራጮችን ለአገር ውስጥና ለውጭ ባለሀብቶች ማስተዋወቅ ዓላማው ያደረገ የኢንቨስትመንት ማስተዋወቂያ መድረክ ባለፈው ሳምንት በሐዋሳ ከተማ መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን፣ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚና የበላይነህ ክንዴ ቢዝነስ ግሩፕ ባለቤትን ጨምሮ ከ106 በላይ ባለሀብቶች በፓርኩ ገብተው ለማልማት ፍላጎታቸውን ገልጸዋል ተብሏል፡፡

በመድረኩ የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ የተለያዩ የግብርና ምርቶችን ከአርሶ አደሩ በመቀበል የአቮካዶ ዘይት፣ ወተት፣ ማርና ቡናን በማቀነባበር ለአገር ውስጥና ውጭ ገበያ የሚያቀርቡ ፋብሪካዎችን ወደ ተግባር ማስገባቱ የተገለፀ ሲሆን ለአብነትም በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ፓርኩ ውስጥ የሚገኙት ፋብሪካዎች ወደ ውጭ ከላኩት ምርት 2.6 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ከመገኘቱም ባሻገር ከ140 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ አርሶ አደሮች የገበያ ትስስር መፍጠሩ ተጠቁሟል፡፡

via - reporter