Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ ቴሌኮም የኢንተርኔት መቆራረጥ ችግር እንደሚኖር ገለፀ። ኢትዮ ቴሌኮም ምሽቱን ለደንበኞቹ | ሰሌዳ | Seleda

ኢትዮ ቴሌኮም የኢንተርኔት መቆራረጥ ችግር እንደሚኖር ገለፀ።

ኢትዮ ቴሌኮም ምሽቱን ለደንበኞቹ ባስተላለፈው መልዕክት “ከሀገር ውጪ (በጅቡቲ) በኩል በሚያልፉ የኢንተርኔት መገናኛ መስመር ላይ ባጋጠመ ችግር” ባለው ምክንያት የኢንተርኔት አገልግሎቱ ሊቆራረጥ ይችላል ብሏል።

በአሁን ሰዓት የኢንተርኔት አገልግሎቱ በመጠባበቂያ መስመሮች ብቻ እየሰራ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን አገልግሎቱን ለማስቀጠል ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል። ችግር የተፈጠርበት መስመር ከፍተኛ ባንድዊድዝ ተሸካሚ ዓለም አቀፍ ባህር ጠለቅ የኢንተርኔት መገናኛ መስመር መሆኑንም ኩባን ያው ገልጿል።