Get Mystery Box with random crypto!

ሰሌዳ | Seleda

የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የሰርጥ አድራሻ: @seledadotio
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.39K
የሰርጥ መግለጫ

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@seleda_support ለማንኛውም አይነት ጥያቄ

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 148

2022-11-05 07:31:04
የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም በሦስት ወራት ውስጥ የ9.8 በመቶ እድገት ማሳየቱ ተገለጸ

ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም አጠቃቀም በ9.8 በመቶ ማሳደግ መቻሉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል። ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም፣ በ2015 የበጀት ዓመት የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም አጠቃቀም 65 በመቶ ለማድረስ እየተሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ለበርካታ ዓመታት የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም አጠቃቀም ከ50 በመቶ በታች እንደነበር ታረቀኝ ተናግረዋል። በ2014 የበጀት ዓመት መጨረሻ የኢትዮጵያ የማምረት አቅም አጠቃቀም 42.7 በመቶ የነበረ ሲሆን፣ በ2015 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ሦስት ወራትም ይህንን ምጣኔ ወደ 52.5 በመቶ ማድረስ እንደተቻለ ታረቀኝ ገልጸዋል።

ከአምራች ኢንዱስትሪዎች የጨርቃ ጨርቅ እንዲሁም የምግብና መጠጥ አምራች ዘርፎች ከ60 በመቶ በላይ አጠቃቀም በማሳየት የተሻለ አፈጻጸም ያላቸው ሲሆን፣ የብረታ ብረትና የቆዳ ዘርፎች ደግሞ ዝቅተኛ አፈጻጸም እንዳሳዩ ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።

via - Addis maleda
5.2K views04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 18:09:34
ትዊተር የሠራተኞች ቅነሳ ሊያደርግ ነው

በቅርቡ ግዢው ተፈጽሞ ባለጸጋው ኤሎን መስክ የተረከበው ትዊተር፤ የሚሰናበቱ ሠራተኞቹን በተመለከተ ዛሬ ለተቀጣሪዎቹ ገለጻ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ግዙፉ የማሕበራዊ ትስስር ገጹ በውስጥ የኢሜል መስመሩ ለሠራተኞቹ በላከው መልዕክት ቅነሳው “ትዊተርን በስኬት ለማስጓዝ አስፈላጊ ነው” ሲል አክሏል።

ኩባንያው አክሎም ቢሮው በጊዜያዊነት የሚዘጋ ሲሆን የሠራተኞች የመግቢያ ካርድም ይታገዳል ብሏል። ባለፈው ሳምንት በ44 ቢሊዮን ዶላር የትዊተርን ግዢ ያጠናቀቀው ቢሊየነሩ መስክ፤ የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ይሆናል።ይህ ከመሰማቱ ቀደም ብሎ መስክ ትዊተር ካለው አጠቃላይ ሠራተኛ ግማሽ ያህሉ ወይም 3 ሺህ 700 ሰዎችን የመቀነስ እቅድ እንዳለው የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

via - bbc
6.8K views15:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 16:04:22
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በተሰጣቸው የንግድ ፍቃድ መሠረት ባልሰሩ 19 ድርጅቶች ላይ እርምጃ ወሰደ፡፡

በመጀመሪያው ሩብ ዓመት  በ206 ድርጅቶች ላይ ባደረገው  የድህረ ፈቃድ ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ተግባር 19 ሚሆኑት ድርጅቶች በተሰጣቸው የንግድ ፍቃድ መሠረት እየሰሩ አለመሆኑ ተመላክቷል፡፡

በዚህም መሠረት በአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ በተደረገው ማጣራት በ11 ድርጅቶች ላይ የንግድ ስራ ፍቃድ እግዳ በ8ቱ ላይ የጽሁፍ ማስጠንቀቅያ እርምጃዎች ተወስዶባቸዋል፡፡ በአንጻሩ 187 ድርጅቶች በህግ አግባብ መሠረት እየሰሩ መሆኑን ሚኒሥቴሩ ገልጿል፡፡

ኢ.ፕ.ድ
6.9K views13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 13:31:25
ባለፉት 3 ወራት ከቡና ሻይና ቅመማቅመም 428 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ።

ባለፉት ሶስት ወራት ከቡና ሻይና ቅመማቅመም 428 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የ2015 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀሙን በጎንደር ከተማ እገመገመ ነው።

በመድረኩ የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ እደተናገሩት ÷ የቡና ሻይና ቅመማቅመም ምርትን ጥራት ለማሳደግና ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለመጨመር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው። ከውጪ ንግድ ግብይት ከተገኘው ገቢ የቡና ድርሻ 426 ሚሊየን ዶላሩን እንደሚሸፍን ነው ዳይሬክተሩ ያስረዱት። በቀጣይ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በክልሎች መካከል የልምድ ልውውጥ ለማካሄድ በትኩረት እንደሚሰራም ተመላክቷል፡፡

via - fbc
6.9K views10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 12:02:31
8ኛው አፍሪካ ሶርሲንግና ፋሽን ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት በስካይ ላይት ሆቴል ተጀመረ።

ለአራት ቀናት የሚቆየው ዓለም አቀፍ አምራቾች የሚሳተፉበት 8ኛው አፍሪካ ሶርሲንግና ፋሽን ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት በስካይ ላይት ሆቴል ተጀምሯል።በንግድ ትርዒቱ የጥጥ፣ የጨርቃ ጨርቅ፣ የቆዳና የቴክኖሎጂ ምርቶች ለእይታ እንደሚቀርቡ ተገልጿል።

የንግድ ትርዒቱን  የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ አምራቾች ማህበር ከመሴ ፍራንክፈርት ግሩፕ ጋር በመተባበር  ነው ያዘጋጁት፡፡ ከ30 በላይ ሀገራት የተውጣጡ ዓለም አቀፍ አምራቾች የሚሳተፉበት የንግድ ትርዒቱ አምራቹን በዓለም ዙሪያ ካሉ በርካታ የንግድ ባለሙያዎች እና ግብዓት አቅራቢዎች ጋር እንደሚያገናኝ ታምኖበታል።
6.6K views09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 11:09:09
በአዲስ አበባ ከተማ  የመታወቂያ እድሳት አገልግሎት ከህዳር 1 ቀን 2015 ዓ.ም  ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች  እንደሚጀመር  ተገለፀ።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ በመጪው ሳምንት ለሚጀመረው የመታወቂያ እድሳት በየደረጃው ያለው መዋቅር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑን ገልፀዋል።

በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የአገልግሎት  መስጫ ማእከላት ቀደም ተብሎ በተከናወነው የቅድመ ዝግጅት ተግባርና አሰራሩ መሰረት አገልግሎት ፈላጊውን ህብረተሰብ በቀናነትና በቅልጥፍና  ማስተናገድ እንደሚገባቸውም አሳስበዋል።
822 views08:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 07:17:50
የታሸገ ውሃ አምራቾች ቀለም አልባ ፕላስቲክን በመጠቀማቸው በአመት 50 ሚሊዮን ዶላር ወጪን እንደሚያስቀር ተገለፀ።

የውኃ ማሸጊያ ፕላስቲክ ጠርሙስ ከሰማያዊ ወደ ነጭ ቀለም መቀየሩ ሀገራችን ለማቅለሚያ ጥሬ እቃው በዓመት ታወጣ የነበረውን ከ50 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ የውጭ ምንዛሬ ማዳን እንደሚቻል የኢትዮጵያ በቨሬጅስ አምራች ኢንዱስትሪዎች ማህበር ቦርድ ፕሬዘዳንት ጌትነት በላይ (ኢንጂነር) ገልጸዋል፡፡

ፕሬዘዳንቱ አክለውም የውኃ የፕላስቲክ ጠርሙስ ነጭ መሆኑ ለጨርቃጨርቅ ማምረቻ ግብዓት የሚሆን ፓሊስተር፣ ፋብሪክና ያርን በሰፊው በማምረት ከውጭ የሚመጣውን ሀገር ውስጥ በመተካት በዓመት ውስጥ ከ45-50ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን ያስችላል ብለዋል፡፡

ነጭ የፕላስቲክ ጠርሙሱ ተፈጭቶና ፕሮሰስ ተደርጎ ወደ ውጭ ኤክስፖርት ሲደረግ ቀድሞ ከነበረው (ማስተርባች) በዓመት ውስጥ በአማካይ በአንድ ቶን እስከ 15 የአሜሪካን ዶላር ተጨማሪ ገቢ እንደሚያስገኝ ኢንጅነር ጌትነት ገልፀዋል፡፡

via - Ethiopian ministry of industry
3.5K views04:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-03 19:27:26
በደቡብ ሱዳን ስምንት ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ የርሃብ አደጋ አንዣቦበታል ተባለ።

በእድሜ ትንሿ ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ደቡብ ሱዳን ስምንት ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝቧ የርሃብ አደጋ እንዳንዣበበት የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት፣ የዓለም ምግብ ፕሮግራም እና ዩኒሴፍ ዛሬ በጋራ ባወጡት ሪፖርት አስጠንቅቋል። በከፍተኛ የምግብ እጥረት የተጠቁና ለከፍተኛ የምግብ እጥረት የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር በርስበርስ ጦርነቱ ወቅት ከነበረው ሁሉ የከፋ እንደሆነ ሪፖርቱ ገልጧል።

ሪፖርቱ የምግብ ዕርዳታ ባስቸኳይ ካልቀረበ፣ ከሚያዝያ እስከ ሐምሌ ባሉት ወራት 7.7 ሚሊዮን ሕዝብ ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ይጋለጣል፤ 1.4 ሚሊዮን ሕጻናትም ለሕይወት አስጊ ለሆነ የምግብ እጥረት ይዳረጋሉ ብሏል። እንደ ሪፖርቱ ከሆነ በአገሪቱ ለከባድ ርሃብ ስጋት የሆኑት፣ ግጭት፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የኢኮኖሚ ችግርና ከፍተኛ የምግብ ዋጋ ንረት ናቸው።
6.0K views16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-03 18:04:26
በሶስት ወራት ውስጥ ብቻ ከግማሽ ሚልየን ሊትር በላይ ነዳጅ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር መያዙ ተገለፀ

ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ500 ሺህ በላይ ሊትር ነዳጅ መያዙን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል። ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው በ2015 ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በህገወጥ መንገድ ግብይት ላይ ሊውል የነበረ ነዳጅ እና ሲሚንቶ መያዝ መቻሉን ገልጿል።

በኦሮሚያ ክልል 49,520 ሊትር ነዳጅ የተያዘ ሲሆን በአማራ ክልል ወደ 40 ሺህ ሊትር የሚጠጋ፣ በሶማሌ ክልል ከ12 ሺህ ሊትር በላይ እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ ከ39 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ በህገወጥ መልኩ ሲዘዋወር ተይዟል።

በህገወጥ ድርጊቱ ተሳታፊ የሆኑ አካላት ላይ ድርጅት ከማሸግ እስከ ምርት የመውሰድ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆናቸውን ያስታወቀው ሚኒስቴሩ በተመሳሳይ በሩብ ዓመቱ በህገወጥ መልኩ ሲዘዋወር የነበረ ከ71 ሺህ ኩንታል በላይ ሲሚንቶ መያዙንና ከዚህም ውስጥ ከ70 ሺህ የሚበልጠው ኩንታል ሲሚንቶ ተወርሶ በመንግስት ተመን ለህብረተሰቡ እንዲሸጥ የተደረገ ሲሆን ቀሪው 674 ኩንታል ሲሚንቶ በህግ ሂደት ላይ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
700 views15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-03 16:47:42
ተዘግቶ የቆየው የማዕድን ግልፅነት ጽሕፈት ቤት እንዲከፈት ተጠየቀ

ከአሥር ዓመታት በፊት በማዕድን ሚኒስቴር ሥር የተቋቋመው የኢትዮጵያ ማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢንሼቲቭ ጽሕፈት ቤት መዘጋት ክፍተት እየፈጠረ ነው በማለት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ኅብረት (ኢሰመድኅ) እንዲከፈት ጠይቋል፡፡ ኅብረቱ የማዕድን ቁፋሮና ማውጣት ዘርፍ ላይ ጥናት ካደረገ በኋላ ነው በድጋሚ ፅህፈት ቤቱ እንዲደራጅ የጠየቀው፡፡

የአምራች ኢንዱስትሪዎች ግልጽነት ኢኒሼቲቭ በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ፣ ጋዝና ማዕድን ሀብት መልካም አስተዳደርን የሚያሰፍን እንዲሁም በዘርፉ ውስጥ ያሉትን ዋና ዋና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የሚንቀሳቀስ ኢኒሼቲቭ መሆኑን ጥናቱ ያመላከተ ሲሆን መንግሥት ይህንን ጽሕፈት ቤት በድጋሚ እንዲያደራጅ እንዲሁም የሲቪል ማኅበራት ተሳትፎ እንዲጨምር ማድረግ እንደሚገባው ኅብረቱ ይፋ ባደረገው ጥናት ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉን ኢኒሼቲቭ ከ2007 ዓ.ም. ጀምሮ አብራ በመሆን የተቀላቀለች ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ያለውን ብሔራዊ ኢንሺቴቭ ጽሕፈት ቤት የማዕድን አውጪዎችን ተጠያቂነት በማስፈን፣ የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ፣ የማዕድን ሚኒስቴር የኢኒሼቲቩን የማረጋገጫ ሪፖርት በማዘጋጀት የባለድርሻ አካላት ውይይትና መረጃ የማሠራጨት ሥራዎችን ይሠራ እንደነበር ሪፖርተር ፅፏል፡፡
2.2K views13:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ