Get Mystery Box with random crypto!

የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም በሦስት ወራት ውስጥ የ9.8 በመቶ እድገት ማሳየቱ ተገለጸ። ባለ | ሰሌዳ | Seleda

የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም በሦስት ወራት ውስጥ የ9.8 በመቶ እድገት ማሳየቱ ተገለጸ

ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም አጠቃቀም በ9.8 በመቶ ማሳደግ መቻሉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል። ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም፣ በ2015 የበጀት ዓመት የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም አጠቃቀም 65 በመቶ ለማድረስ እየተሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ለበርካታ ዓመታት የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም አጠቃቀም ከ50 በመቶ በታች እንደነበር ታረቀኝ ተናግረዋል። በ2014 የበጀት ዓመት መጨረሻ የኢትዮጵያ የማምረት አቅም አጠቃቀም 42.7 በመቶ የነበረ ሲሆን፣ በ2015 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ሦስት ወራትም ይህንን ምጣኔ ወደ 52.5 በመቶ ማድረስ እንደተቻለ ታረቀኝ ገልጸዋል።

ከአምራች ኢንዱስትሪዎች የጨርቃ ጨርቅ እንዲሁም የምግብና መጠጥ አምራች ዘርፎች ከ60 በመቶ በላይ አጠቃቀም በማሳየት የተሻለ አፈጻጸም ያላቸው ሲሆን፣ የብረታ ብረትና የቆዳ ዘርፎች ደግሞ ዝቅተኛ አፈጻጸም እንዳሳዩ ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።

via - Addis maleda