Get Mystery Box with random crypto!

ትዊተር የሠራተኞች ቅነሳ ሊያደርግ ነው በቅርቡ ግዢው ተፈጽሞ ባለጸጋው ኤሎን መስክ የተረከበው | ሰሌዳ | Seleda

ትዊተር የሠራተኞች ቅነሳ ሊያደርግ ነው

በቅርቡ ግዢው ተፈጽሞ ባለጸጋው ኤሎን መስክ የተረከበው ትዊተር፤ የሚሰናበቱ ሠራተኞቹን በተመለከተ ዛሬ ለተቀጣሪዎቹ ገለጻ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ግዙፉ የማሕበራዊ ትስስር ገጹ በውስጥ የኢሜል መስመሩ ለሠራተኞቹ በላከው መልዕክት ቅነሳው “ትዊተርን በስኬት ለማስጓዝ አስፈላጊ ነው” ሲል አክሏል።

ኩባንያው አክሎም ቢሮው በጊዜያዊነት የሚዘጋ ሲሆን የሠራተኞች የመግቢያ ካርድም ይታገዳል ብሏል። ባለፈው ሳምንት በ44 ቢሊዮን ዶላር የትዊተርን ግዢ ያጠናቀቀው ቢሊየነሩ መስክ፤ የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ይሆናል።ይህ ከመሰማቱ ቀደም ብሎ መስክ ትዊተር ካለው አጠቃላይ ሠራተኛ ግማሽ ያህሉ ወይም 3 ሺህ 700 ሰዎችን የመቀነስ እቅድ እንዳለው የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

via - bbc