የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በተሰጣቸው የንግድ ፍቃድ መሠረት ባልሰሩ 19 ድርጅቶች ላይ እርምጃ ወሰደ፡፡ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በ206 ድርጅቶች ላይ ባደረገው የድህረ ፈቃድ ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ተግባር 19 ሚሆኑት ድርጅቶች በተሰጣቸው የንግድ ፍቃድ መሠረት እየሰሩ አለመሆኑ ተመላክቷል፡፡ በዚህም መሠረት በአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ በተደረገው ማጣራት በ11 ድርጅቶች ላይ የንግድ ስራ ፍቃድ እግዳ በ8ቱ ላይ የጽሁፍ ማስጠንቀቅያ እርምጃዎች ተወስዶባቸዋል፡፡ በአንጻሩ 187 ድርጅቶች በህግ አግባብ መሠረት እየሰሩ መሆኑን ሚኒሥቴሩ ገልጿል፡፡ ኢ.ፕ.ድ 6.9K views13:04