Get Mystery Box with random crypto!

በ2030 ቻይና የአለም ኢኮኖሚ ቁንጮ ልትሆን እንደምትችል አይ ኤም ኤፍ ጠቆመ። ዓለም አቀፉ የ | ሰሌዳ | Seleda

በ2030 ቻይና የአለም ኢኮኖሚ ቁንጮ ልትሆን እንደምትችል አይ ኤም ኤፍ ጠቆመ።

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ.ኤም.ኤፍ.) ሊጠናቀቅ የተቃረበውን የፈረንጆቹን አመት የአለም የኢኮኖሚ ድርሻ በጥናቱ ይፋ ሲያደርግ አሜሪካ አሁንም ትልቁን ድርሻ ይዛለች። በአለም ላይ የተፈጠረው ግጭትና ግርግር እንዲሁም የዋጋ ንረት የዓለም ኢኮኖሚን ወደ 104 ትሪሊዮን ዶላር ከፍ እንዳደረገው ተቋሙ ገልጿል።

እንደ ተቋሙ ጥናት ከሆነ ከመቶ ትሪሊዮን የአለም ኢኮኖሚ አሜሪካ አንድ አራተኛውን ($25.3 ትሪሊዮን) ስትይዝ በቅርብ ርቀት የምትከተላት ቻይና $19.9 ትሪሊዮን ጂዲፒ ማስመዝገቧን አሳውቋል። አሜሪካ የአለም ኢኮኖሚን ከ1871 ጀምሮ በበላይነት ስትመራ መቆየቷን ያነሳው ጥናቱ ይህ ግን ማብቂያው እየተቃረበ ስለመሆኑ ጠቁሟል። ነገሮች በዚሁ ሁኔታ ሚቀጥሉ ከሆነ በ2030 መሪነቱን በቻይና ልትነጠቅ እንደምትችል ነው ያሳወቀው።

ጥናቱ አክሎም በአመቱ አየርላንድ ከአውሮፓ በጣም ፈጣን የተባለውን የኢኮኖሚ እድገት በ5.2 በመቶ ስታስመዘግብ እንደ ቱቫሉ ያሉ የእስያ ክልሎች ደግሞ ዝቅተኛ ጂዲፒን አስመዝግበዋል።

via - IMF