Get Mystery Box with random crypto!

ሰሌዳ | Seleda

የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የሰርጥ አድራሻ: @seledadotio
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.39K
የሰርጥ መግለጫ

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@seleda_support ለማንኛውም አይነት ጥያቄ

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 144

2022-11-11 18:54:06
የእንግሊዝኛ ቋንቋን ያለምንም የበይነ መረብ ክፍያ ለመማር የሚያስችል መማሪያ ይፋ ሆነ።

የእንግሊዝኛ ቋንቋን ያለምንም የበይነ መረብ ክፍያ ለመማር የሚያስችል መማሪያ  የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የኢትዮ-ቴሌ ኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬ ህይወት ታምሩ በተገኙበት ይፋ ሆኗል:: መማሪያው በትምህርት ሚኒስቴር የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የተዘጋጀ ሲሆን ከተማሪዎችና መምህራን በተጨማሪ ሁሉም የማህበረሰብ አካል ሊጠቀምበት እንደሚችል ተጠቁሟል::

የኢትዮ-ቴሌ ኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬ ህይወት ታምሩ በበኩላቸው ትውልድን የመገንባት ሃላፊነት የጋራ በመሆኑ መማሪያው ያለምንም የበይነ መረብ ክፍያ አገልግሎት ላይ እንዲውል ማድረጋችን ማህበራዊ ሃላፊነታችንን የምንወጣበት አንዱ ማሳያ ነው  ያሉ ሲሆን የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እያከናወናቸው ያሉትን የለውጥ ስራዎች ኢትዮ ቴሌኮም እንደሚደግፍ ተናግረዋል።
5.2K views15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 16:04:48
የማዕድን ሚኒስቴር የማዕድን ምዘናና የምርምር ላቦራቶሪ ለመገንባት ከኤስ ጂ ኤስ ግሩፕ ጋር ተፈራረመ።

ላቦራቶሪው በ2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ወጪ የሚገነባ መሆኑን የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። ማዕከሉ የማዕድን ክፍለ ኢኮኖሚ ችግርን የሚፈታና የሀገራችን የማዕድን ጥራትን በማሳደግ በዓለም የማዕድን ገበያ ተፎካካሪነትን የሚጨምር ነው ተብሏል።

የማዕድን ሚኒስቴር ትናንት ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በሚሊኒየም አዳራሽ በተከፈተው በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ እያካሄደው ባለው ኤክስፖ ከ270 በላይ ኩባንያዎች እየተሳተፉ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም ዛሬ ኤክስፖውን ጎብኝተዋል።
5.8K views13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 14:22:43
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን የግል ባለሃብቶች በአቪየሽን መስክ መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቀረበ፡፡

በአቪየሽን መስክ የግል ባለሃብቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችሉ የፖሊሲ እና ህግ ማሻሻያዎች መደረጋቸውን የገለፁት የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው መንግስቴ፣ ባለሃብቶች ከአየር ትራንስፖርት አገልግሎት በተጨማሪ በአውሮፕላን ጥገና፣ በኤሮስፔስ ምርት፣ ካርጎ እና ሎጅስቲክስ፣ በባለሙያ ሥልጠና እንዲሳተፉ ክፍት መደረጉን ገልፀዋል፡፡

አቶ ጌታቸው የግሉ ዘርፍ በኤርፖርት ልማት፣ በአየር ማረፊያ (Airtsrip) እና ሄሊኮፕተር ማረፊያ (Helipad) ግንባታ እንዲሳተፍ የሚያስችል ማሻሻያ መደረጉን የገለፁት የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ሲቪል አቪየሽን ድርጅት ምክር ቤት አባል ሆና መመረጧን አስመልክቶ አስመልክቶ ትላንት በስካይ ላይት ሆቴል እውቅና ፕሮግራም ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡

ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ
6.2K views11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 12:28:41
የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን ለማጓጓዝ መዘጋጀቱን አስታወቀ።

የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አብዲ ዘነበ እንደገለጹት፤ የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት የአገሪቷን ገቢ በመጨመር በኩል አወንታዊ ሚና እያበረከተ ነው። በተለይም ወሳኝ የሆኑ ምርቶች በማጓጓዝ በኩል ውጤታማ ስራ አከናውኗል።

ለአብነትም ባለፈው በጀት ዓመት የአገሪቷ ዋነኛ የወጪ ምርት የሆነው ቡና ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የተጓጓዘው በኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር በኩል መሆኑን ጠቅሰዋል። በተጨማሪም 55 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ወደ አገር ውስጥ ማጓጓዝ መቻሉን ጠቅሰው፤ የአፈር ማዳበሪያን ሎጂስቲክስ በማሳለጥ ረገድም የተሻለ ስራ ተከናውኗል ነው ያሉት። በዚህም ለሎጅስቲክስ ይወጣ የነበረን 1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ማዳን መቻሉን ጠቅሰዋል።

የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት የሚሰጠውን አገልግሎት ለማስፋት የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸው፤ በዚህም ማቀዝቀዣ በተገጠመላቸው ዋገኖች አማካኝነት አትክልትና ፍራፍሬን ጨምሮ ሌሎች ተጨማሪ ምርቶችን ለማጓጓዝ እንቅስቃሴ ተጀምሯል ብለዋል። ከቱሪዝም ጋር በተያያዘም ኢትዮጵያን እንዲሁም ጅቡቲን መጎብኘት ለሚፈልጉ አካላት የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት እንቅስቃሴ መጀመሩን ኢዜአ ዘግቧል።
1.8K views09:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 10:45:51
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ሳምንት የደንበኞቹን ቁጥር አንድ ሚልየን እንደሚገባ ገለፀ።

የሳፋሪኮም ኩባንያ ዛሬ የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት በናይሮቢ በቀረበበት መድረክ የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፒተር ንዴግዋ “በኬንያ እና በኢትዮጵያ እንደ የዋጋ ግሽበት፣ የምንዛሪ ዋጋ ማሽቆልቆል እና ፈጣን ያልሆነ የሀገር ውስጥ ምርት ዕድገት የመሳሰሉ ከማክሮ ኢኮኖሚ ጋር የተያያዙ ተግዳርቶች አጋጥመውናል” ብለዋል።

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ አንዋር ሶሳ ከአዲስ ዘይቤ ለቀረበላቸው ጥያቄ በመድረኩ እንደተናገሩት ከነሐሴ 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ከ933 ሺህ ደንበኛ ማፍራት ተችሏል ብለዋል። “ቁጥሩ በየጊዜው የሚቀያየር ነው፤ እስካሁን ባለው ሁኔታ ከ900 ሺህ የተሻገርን ሲሆን በሚቀጥለው ሳምንት አንድ ሚልየን ደንበኞች እንደርሳለን” ሲሉ ዋና ስራ አስፈፃሚው አንዋር ሶሳ ተናግረዋል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሀገሪቱ ያሉ ሁኔታዎችን ታሳቢ ያደረገ ስራ መስራቱን ይቀጥላል ያሉት አንዋር ሶሳ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ከጦርነቱ ነፃ የሆኑ አካባቢዎችን ለመድረስ እቅድ አለን ብለዋል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. በድሬደዋ ከተማ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ የሚታወስ ነው።

via - Addis zeybe
3.3K views07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 09:48:22
#ለጥንቃቄ

ክራውድ ዋንን በተመለከተ #Share ይደረግ የኤልያስ መሰረት መልዕክት ነው።

ክራውድ ዋን (Crowd 1) የተባለ የኦንላይን እንቅስቃሴ በሀገራችን በሰፊው እየተስተዋለ ነው። ድርጅቱ የዛሬ ሁለት አመት "የትምህርት ፓኬጆች እንሸጣለን" ይል የነበረ ሲሆን ዛሬ ደግሞ "ሜታቨርሲ፣ ሚግስ ኤስ ተር እና ፕላኔት አይ ኤክስ" የተባሉ ምርቶችን እናቀርባለን ይላል። እነዚህ ምርቶች ኦላይን ጌሞች፣ ኦላይን ቪርቹዌል ፕረዘንስ... እንደሆኑ ሰዎቹ ያስረዳሉ። ለዚህም 129 ዩሮ፣ 319 ዩሮ እና 819 ዩሮ በየደረጃው ይከፈላል።

ስለ ድርጅቱ የተገኘው መረጃ ይህ ነው

የክራውድ ዋን ባለቤት Impact Crowd Technology (ICT) የተባለ ኩባንያ ሲሆን Tor Anders Petteroe የተባለ ግለሰብ ደግሞ አንቀሳቃሹ ነው። ይህ ግለሰብ ብዙ ሚልዮን ዶላሮችን ካገኘ በኋላ ግን ከስሬያለሁ በማለት (bankruptcy declare በማድረግ) ድርጅቶቹን ዘግቷል።

Crowd 1 ድርጅትን በቀጥታ የመሰረተው ደግሞ Jonas Eric Werner የሚባል የፖንዚ ስኪም በማከናወን የሚታወቅ ግለሰብ ነው። የዛሬ አስር አመት ገደማ Synkronice/Spinglo የተባለ የአጭበርባሪ ድርጅት ከፍቶ ሗላ ላይ ዘግቷል። ክራውድ ዋን በኖርዌይ፣ በፊሊፒንስ፣ በናሚቢያ፣ በቡሩንዲ ወዘተ የታገደ ድርጅት ነው። ከዚህ ድርጅት እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ 17 ሰዎች ቡሩንዲ ውስጥ ለእስር ተዳርገዋል።

ብዙ ሰው በኑሮ ውድነት በሚጨነቅበት በዚህ ወቅት እንዲህ አይነት የማጭበርበር ድርጊት በስርዐቱ ተጣርቶ መረጃው ለህዝብ ሊገለፅ ይገባል። አለበለዛ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች እንደ ፊያስ ከተጭበረበሩ በሗላ ዜና መስራት ዋጋ የለውም።

Via:-EliasMeseret
3.6K views06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 07:25:21
ኢትዮጵያ በበይነ መረብ ተጠቃሚዎች ብዛት ከአፍሪካ አገራት አምስተኛ ደረጃን ያዘች።

ምጣኔ ሀብታቸው በቴክኖሎጂ አማካኝነት ፈጣን እድገት እያሳዩ ካሉ አህጉራት አንዷ በሆነችው አፍሪካ በፈረንጆች 2022፣ ናይጀሪያ በበይነ መረብ ተጠቃሚዎች ብዛት ቀዳሚዋ ነች ይላል ቢዝነስ ኢንሳይደር አፍሪካ። በዚህም ከ51 በመቶ በላይ የናይጄሪያ ህዝብ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ነው ተብሏል።

ግብፅ እና ደቡብ አፍሪካ ተካታዮቹ ሲሆኑ፣ አገራችን ኢትዮጵያ 29 ሚሊዮን በላይ የበይነ መረብ ተጠቃሚዎችን በመያዝ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። የኢትዮጵያ የበይነ መረብ ተደራሽነት 25 በመቶ ሲሆን፣ ሞሮኮ 84 በመቶ በመያዝ ቀዳሚዋ የበይነ መረብ ተደራሽነት ያለባት አገር ነች።

ምንጭ፡-ቢዝነስ ኢንሳይደር አፍሪካ
4.4K views04:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 20:18:17
ሕብረት ባንክ “ሕብር ኢ-ኮሜርስ” የተሰኘ የኤሌክትሮኒክ ክፍያ አገልግሎት ይፋ አደረገ።

በማስተር ካርድ የክፍያ ጌትዌይ የሚሰራው “ሕብር ኢ-ኮሜርስ” የተሰኘው በኢትዮጵያ የሚገኙ የንግድ ድርጅቶች  ምርቶቻቸውን ኦንላይን ለዓለም አቀፍ ደንበኞች እንዲሸጡና አዳዲስ ደንበኞችንም እንዲያገኙ ያስችላል ተብሏል፡፡

“ሕብር ኢ-ኮሜርስ” በኢትዮጵያ  የሚገኙ የንግድ ተቋማትና ነጋዴዎች በማስተር ካርድና በሌሎች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸው ካርዶች ክፍያ ከኢትዮጵያ ውጭ ካሉ ደንበኞች መቀበል እንዲችሉ የሚረዳ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

ስርዓቱ የሀገር ውስጥ ንግዶች አዳዲስ ዓለም አቀፍ ገበያዎችን ማግኘት እንዲችሉና ገቢያቸው እንዲያድግ ብሎም ኢትዮጵያ በዲጂታል ኢኮኖሚው ገበያ እንዲኖራት የሚያግዝ መሆኑም ተገልጿል፡፡
1.7K views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 18:38:01
ኤምሬትስ አየር መንገድ በግማሽ ዓመት ክብረ ወሰን የሰበረ ትርፍ አገኘ።

የረጅም ርቀት ትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ የሆነው ኤምሬትስ አየር መንገድ በዚህ ዓመት ክብረ ወሰን የሰበረ የግማሽ ዓመት ትርፍ 1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር እንዳገኘ ኩባንያው አስታውቋል። አየር መንገዱ ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ላይ የአንድ ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ቢያስመዘግብም ከዚህ ኪሳራ በኋላ ትልቅ ለውጥን አምጥቷል ተብሏል።

ኤሚሬትስ ቡድን አየር መንገዱን፣ የዲናታ ኤርፖርት አገልግሎት ድርጅትን እና ሌሎች ኩባንያዎችን ጨምሮ 15 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ የነበረው ሲሆን፤ ባለፈው ዓመት 6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን ኤቢሲ ኒውስ ዘግቧል። ኤሚሬትስ ከሚያዝያ እስከ መስከረም ወር መጨረሻ ድረስ 20 ሚሊዮን መንገደኞችን ማጓጓዙንም አሳውቋል።

via - Alain
3.2K views15:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 16:37:44
ጎሕ ቤቶች ባንክና የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በጋራ ለመስራት ተስማሙ።

ስምምነቱን የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ አስማረ እና የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ የተፈራረሙት ሲሆን በተቋማቱ መካከል ያሉ የውክልና፣ የሽያጭና ሌሎች ተጓዳኝ የሰነድ አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ በሆነ የኦንላይን አማራጭ ለማከናወን የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈም የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ያረጋገጣቸውንና የመዘገባቸውን ሰነዶች ባንኩ በቅርንፎቹ መጠቀም የሚችልበት ቀላል አማራጭ በመሆኑ ለተገልጋዮቹ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡በጥቅምት ወር 2014 ዓ.ም ስራ የጀመረው ጎሕ ቤቶች ባንክ ከ5 ሺህ 800 በላይ ደንበኞችን ማፍራት መቻሉ ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡
4.3K views13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ