Get Mystery Box with random crypto!

ሕብረት ባንክ “ሕብር ኢ-ኮሜርስ” የተሰኘ የኤሌክትሮኒክ ክፍያ አገልግሎት ይፋ አደረገ። በማስተ | ሰሌዳ | Seleda

ሕብረት ባንክ “ሕብር ኢ-ኮሜርስ” የተሰኘ የኤሌክትሮኒክ ክፍያ አገልግሎት ይፋ አደረገ።

በማስተር ካርድ የክፍያ ጌትዌይ የሚሰራው “ሕብር ኢ-ኮሜርስ” የተሰኘው በኢትዮጵያ የሚገኙ የንግድ ድርጅቶች  ምርቶቻቸውን ኦንላይን ለዓለም አቀፍ ደንበኞች እንዲሸጡና አዳዲስ ደንበኞችንም እንዲያገኙ ያስችላል ተብሏል፡፡

“ሕብር ኢ-ኮሜርስ” በኢትዮጵያ  የሚገኙ የንግድ ተቋማትና ነጋዴዎች በማስተር ካርድና በሌሎች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸው ካርዶች ክፍያ ከኢትዮጵያ ውጭ ካሉ ደንበኞች መቀበል እንዲችሉ የሚረዳ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

ስርዓቱ የሀገር ውስጥ ንግዶች አዳዲስ ዓለም አቀፍ ገበያዎችን ማግኘት እንዲችሉና ገቢያቸው እንዲያድግ ብሎም ኢትዮጵያ በዲጂታል ኢኮኖሚው ገበያ እንዲኖራት የሚያግዝ መሆኑም ተገልጿል፡፡