Get Mystery Box with random crypto!

ጎሕ ቤቶች ባንክና የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በጋራ ለመስራት ተስማሙ። ስምምነቱን | ሰሌዳ | Seleda

ጎሕ ቤቶች ባንክና የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በጋራ ለመስራት ተስማሙ።

ስምምነቱን የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ አስማረ እና የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ የተፈራረሙት ሲሆን በተቋማቱ መካከል ያሉ የውክልና፣ የሽያጭና ሌሎች ተጓዳኝ የሰነድ አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ በሆነ የኦንላይን አማራጭ ለማከናወን የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈም የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ያረጋገጣቸውንና የመዘገባቸውን ሰነዶች ባንኩ በቅርንፎቹ መጠቀም የሚችልበት ቀላል አማራጭ በመሆኑ ለተገልጋዮቹ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡በጥቅምት ወር 2014 ዓ.ም ስራ የጀመረው ጎሕ ቤቶች ባንክ ከ5 ሺህ 800 በላይ ደንበኞችን ማፍራት መቻሉ ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡