Get Mystery Box with random crypto!

የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ እንዲሰሩ መፈቀዱ የፋይናንስ ተወዳዳሪነትን በማነቃቃት የዘርፉን ተደራሽነት | ሰሌዳ | Seleda

የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ እንዲሰሩ መፈቀዱ የፋይናንስ ተወዳዳሪነትን በማነቃቃት የዘርፉን ተደራሽነት ይጨምራል - ኤርሚያስ አመልጋ

በኢትዮጵያ እስከ 1970ዎቹ ድረስ የጣሊያንና የህንድን ጨምሮ የሌሎች አገራት ባንኮችና የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በአገር ውስጥ ይንቀሳቀሱ እንደነበር ይታወሳል። ሆኖም በወቅቱ ኢትዮጵያ ትከተለው በነበረው ርዕዮተ ዓለም ምክንያት የውጭ አገራት ዜጎች ባንኮቻቸውን ዘግተው ወደ አገራቸው ለመመለስ ተገደዋል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ለውጭ አካላት ዝግ እንደሆነ ቆይቷል።

የፋይናንስና የኢኮኖሚ ባለሙያው ኤርሚያስ አመልጋ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ስርዓት ለውጭ ባንኮች ዝግ ሆኖ መቆየቱ የፋይናንስ ስርዓቱ እና የምንዛሬ ግብይቱ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን አንስተዋል።
በአሁኑ ወቅት የውጭ አገራት ባንኮች በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ የተከፈተው እድልም እንደ አዲስ ሊታይ እንደማይገባ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ዘግይታም ቢሆን ወደነበረችበት የፋይናንስ አሳታፊ ስርዓት መመለሷ በቴክኖሎጂ፣ በዓለም አቀፍ ንግድና በፋይናንስ መሰረተ ልማት ዕድገት ላይ ጉልህ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ጠቁመዋል። የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ከስራ ዕድል ባለፈ የተሻለ የፋይናንስ ተወዳዳሪነትን ይፈጥራል ብለዋል።

via - ENA