Get Mystery Box with random crypto!

ከአራት ወራት በላይ ተቋርጦ የነበረው የመታወቂያ እድሳት አገልግሎት ጀመረ በአዲስ አበባ ከተማ | ሰሌዳ | Seleda

ከአራት ወራት በላይ ተቋርጦ የነበረው የመታወቂያ እድሳት አገልግሎት ጀመረ

በአዲስ አበባ ከተማ ከአራት ወራት በላይ ተቋርጦ የነበረው የመታወቂያ እድሳት አገልግሎት በዛሬው ዕለት ጀምሯል። የመታውቂያ ዕድሳት አገልግሎት አሰጣጡ ለሕግ ወጥ ድርጊት ተጋልጦ የነበረ በመሆኑ እና የተለያዩ የሰላምና ፀጥታ ስጋት ጭምር በመፍጠሩ አገልግሎቱ መቋረጡ ይታወሳል።

አገልገሎቱ ተድቅኖበት የነበረውን ችግር በማረም እና በማስተካከል ዳግም የመታውቂያ እድሳት በዛሬው ዕለት ተግባራዊ መደረግ መጀመሩን ኤ ኤም ኤን ዘግቧል።